የቀደመውን ጸጸት ተው አዳዲስ ምርጫዎችን አድርግ

የቀደመውን ጸጸት ተው አዳዲስ ምርጫዎችን አድርግ

ስለዚህ ማንም በክርስቶስ ቢሆን አዲስ ፍጥረት ነው፤ አሮጌው ነገር አልፎአል፤ እነሆ፣ አዲስ ሆኖአል። – 2 ቆሮ 5፡17

የተሳሳቱ ምርጫዎች የጸጸት መንስኤ ናቸው፡፡ ጸጸት በሚሰማን ወቅት ጊዜ ትኩረት ልንሰጠው እና በመቀጠል እንዴት አድርገን የተሻሉ ምርጫዎችን ወደ ፊት መምረጥ አንምንችል ልንማርበት ይገባል፡፡

መጀመሪያውኑ የተሳሳቱ ምርጫዎች ለጸጸት እንደሚዳርጉ እረዳለሁ፡፡ ከብዙ አመታት በፊት በእኔ እና በባለቤቴ ዴቭ መካከል ሊታይ የሚችል ልዩነት እንደነበረን አጤንኩ ይህ ደግሞ የሆነው እርሱ በዘመኑ ሁሉ የሰውነት ማጎልመሻ በማዘወተሩ ከእኔ ይልቅ ጤናማ ፣ ጠንካራ እና የሚያምር ተክለሰውነት ስለነበረው ነው፡፡

መጀመርያ ላይ እንደ ዴቭ ጠንካራ ባለመሆኔ እጸጸት ነበር ይሁን እንጂ በግሌ ላደርገው የምችለው ነገር እንዳለ ተረዳሁ፡፡ አሁን የሰውነት ማጎልመሻ እንቅስቃሴዎችን አዘወትራለሁ ባመጣሁትም በጎ ለውጥ እደነቃለሁ፡፡

መጽሀፍ ቅዱስ አዲስ ፍጥረት ናችሁ ይላል፡፡ ባረጀው የሕይወት ልማድ መኖር አቁማችሁ አሁን የተሻለ ፣ አዲስ እና በመንፈስ ቅዱስ አቅምን የታጠቀ ሕይወት መኖር ትችላላችሁ፡፡ አስቀድማችሁ በመረጣችሁት ብልሕነት በጎደለው ምርጫችሁ በጸጸት ውስጥ ገብታችሁ ራሳችሁን ካገኛችሁት ረፍዶብኛል በሚል ሀሳብ አትሞኙ፡፡ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ በመጀመር መጽናት ይጠበቅባችኋል፡፡

የተሻለ ምርጫዎችን መምረጥ ስትጀምሩ እግዚአብሔር ስለ እናተ ያዘጋጀውን በረከቶች በየዕለቱ ትለማመዳላችሁ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ አዲስ ፍጥረት መደረጌን አውቃለሁ ፡፡ በቀደመው ሕይወት በጸጸት ውስጥ መኖር አልፈልግም፡፡ ለእኔ ያለህን የወደፊት ሂወቴን ደስተኛ ማድረግ የሚችለውን መልካም ምርጫዎችን እንድመርጥ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon