የተገራ ሕይወት የእግዚአብሔርን ሰላም ያመጣል

የተገራ ሕይወት የእግዚአብሔርን ሰላም ያመጣል

ቅጣት ሁሉ በወቅቱ የሚያሳዝን እንጂ ደስ የሚያሰኝ አይመስልም፤ በኋላ ግን ለለመዱት ሰዎች የጽድቅና የሰላም ፍሬ ያስገኝላቸዋል። – ዕብራዊያን 12፡11

በርከት ያሉ ጉዳዮች እንደ ጊዜ ፣ ጉልበት እና ትኩረት ያሉ የተገደቡ ሀብቶቻችንን ይሻሙብናል፡፡ የተጣበበ የቀጠሮ መመዝገቢያዬን እያየሁ በእግዚአብሔር ያጉረመረምኩበት ጊዜ ነበር፡፡ ጌታ ሆይ ‹‹እኔ እየሰራሁ ያለሁትን ነገር ለሰው እንዴት ይቻለዋል?›› እልም ነበር፡፡

ቀጠሮዎችን የመዘገብኩት እኔ ነበርኩኝ እና ከእኔ ውጭ ሊያስተካክላቸው የሚችል እንደሌለ ሳስብ ልቦናዬ ተነካ፡፡ ነገሮቼን ማስተካከል የማይቻል ከሆነ በመመኘት ብቻ ጊዜ መውሰድ የለብኝም፡፡ እግዚአብሔር ራሴን በመግራት ሕይወቴን ማቅለል እንዳለብኝ ተናገረኝ፡፡

እናንተም በዚሁ አግባብ ሕይወታችሁን መግራት ይኖርባችኋል፡፡ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳችሁ ጠይቁ፡፡ እርሱም ልትሰጡለት የሚገባውን እና ልትጥሉት የሚገባው የቱ እንደሆነ ያሳያችኋል፡፡ ተገርቶ ለማያውቅ ሰው መጀመር አስቸጋሪ ለሆን ይችላል ይሁን እንጂ በመገራት ውስጥ ባለው ሕመም እና ራስን በመግዛት ውስጥ ያለው ሽልማት ታላቅ ነው፡፡ የመጽሀፍ ቅዱስ ተግሳጽ ሰላምን ያመጣል፡፡

ዛሬ ራሳችሁን ብትገሩ ደስታንና ሰላምን ከእግዚአብሔር ታገኛላችሁ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ በቅጡ ከተገራ ሕይወት የሚገኘውን ሰላም መለማመድ እሻለሁ፡፡ በራሴ ተወጣጥሬ ልፈነዳ በምደርስበት ወቅት እንድረጋጋና ላንተ እንዳደርግ የምትፈልገውን ነገር ብቻ እንዳደርግ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon