የእግዚአብሔርን ኀይል በጸሎት መቀበል

የእግዚአብሔርን ኀይል በጸሎት መቀበል

ኢየሱስ በዚህ ምድር በኖረበት ዘመን ከሚት ሊያድነዉ ወደሚችለዉ ጸሎትንና ልመናን ከታላቅ ጩኸትና ከእንባ ጋር አቀረበ፤ ፍጹም ትሁት ሆኖ በመታዘዙም ጸሎቱ ተሰማለት፡፡ – ዕብ 5:7

ጸሎት እጅግ ሐይለኛ ነዉ ምክንያቱም በምድር ያሉ ሰዎችን ልብ በሰማይ ካለዉ ከእግዚአብሔር ልብ ጋር ያገናኘልና፡፡ ስንጸልይ ከእግዚአብሔር ጋር እንገናኛለን እርሱ የየዕለት ኑሮአችንን ከግምታችን በላይ በሆነ መንገድ ይቀይረዋል፡፡

ጸሎት በመላዉ ህዋ ከሚገኙ ታላላቅ ኀይላት አንዱ እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ያንን ስል ግነት ሊመስል ይችላል ግን እዉነታዉ ይኸዉ ነዉ፡፡

ጸሎት እግዚአብሔር እንዲሰራ በሮችን ይከፍታል፡፡ ጸሎት እኔና እናንተ በምድር ቁጭ ብልን ሰማያዊ ሐይል ወደ ህይወታችን መጥቶ ጥበብን፣ ምሪትን፣ መጽናናትን፣ ወይም ተዓምርን ጥሶ እንዲያወጣ ስንፈልግ የምናከናዉነዉ ተግባር ነዉ፡፡ ጸሎት እኛን ከአግዚአብሔር ሐይል ጋር ስለሚያገናኝ ነዉ ከምንገምተዉ በላይ ታላቅ ሐይል ነዉ ማለታቸን፡፡ ኢየሱስ እንኳን ጸሎት አስፈልጎታል ጸልዮም ሐይል አግኝቷል በምድር ሳለ፡፡

የእግዚአብሔር ሐይል ብቻ ነዉ ሰላምና ደስታን ማምጣት፣ ጥበብ መስጠት፣ ለሰዎች ህይወት ትርጉምና ዓላማ መስጠትና ማንኛዉንም ዓይነት ተዓምራት መስራት የሚችለዉ፡፡
ይህ ሐይል በህይወታችሁ ሲሰራ ማየት ትፈልጋላችሁ? ከሆነ ጸሎትን ቀዳማይ አድርግ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! የጸሎት ሔል አስደናቂ ነዉ እኔም ከአንተ ጋር መገናኘትና ሥራህን በህይወቴ ማየት እፈልጋለሁ፡፡ ከዚህ በኋላ ከአንተ ጋር በጸሎት በቋሚነት ለመገናኘትና ለመቆየት እተጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon