የዓለምን ሳይሆን የእግዚአብሔር መስፈረት ምረጥ

የዓለምን ሳይሆን የእግዚአብሔር መስፈረት ምረጥ

በክፉዎች ምክር የማይሄድ፣ በኀጢአተኞች መንገድ የማይቆም፣ በፌዘኞችም ወንበር የማይቀመጥ፣ ሰው ብፁዕ ነው። – መዝሙር 1፡1

ከምንኖርበት ማህበረሰብ አስተሳሰብ የላቀ ሥነምግባር ተላብሶ መኖር የምርጫ ጉዳይ ነው፡፡ እንዴት እንደምናወራ ፣ ምን እንደምንለብስ ፣ እንደምናነብ ፣ የትኛውን የቴሌቪዥን መርሃ ግብር እንደምንከታተል መምረጥ የላቀ የሥነምግባራችንን ምርጫ ያሳያል፡፡ ይህም በግል ሕይወታችን የምንመራውን ምልዕ ሕይወት ይጠቁማል በተጫመሪም በስራችንም ይሁን በሙያ መስካችን ላይ ይንጸባረቃል፡፡

እንደ ክርስቲያን በየዕለቱ በቅዱስ አኗኗር ልንበረታታ እና የዐለምን ስበት ልንቋቋም ይገባናል፡፡ አንድ የታወቀ አባባል ለዚህ ጥሩ መልዕክት አለው ‹‹ሃሳብህን ጠብቅ ቃላት ይሆናልና ፤ ቃልህ ጠበቅ ድርጊት ይሆናሉ እና ፤ ድርጊትህን ጠብቅ ልማድ ይሆናሉ እና ፤ ልማድህን ጠብቅ ጠባይ ይሆናሉ እና ፤ ጠባይህን ጠብቅ ፍጻሜህን ይወስናሉና፡፡››

አምላክ ለሰው ልጅ ከሰጠው አንዱ ሥጦታ መካከል መምረጥ የሚችልበትን ነጻ ፈቃድ ነው፡፡ አምላክ ለኛ ያለውን ሕይወት ልንደሰትበት ከፈለግን ሕይወታችንን እንደ ፈቃዱ ባለ፣ በቃሉ ውስጥ በሚገኝ እሴት እና ወጥነት ባለው ምርጫ ውስጥ ማኖር ይጠበቅብናል፡፡ በየዕለቱ እየተናደ ባለው የዐለም እሴት እና ምርጫ መያዝ የለብንም፡፡

ይህን አበክሬ እንግራችኋለሁ እግዚአብሔርን በሙላት ለማገልገል አስቀድምን እርሱን የሁሉ ነገራችን መጀመሪያ ለማድረግ መወሰን ያስፈልጋል፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በዚህ ዓለም መርህ መኖር አልፈልግም፡፡ አቤቱ የአንተ መንገድ ከሁሉ የሚሻል ነውና አንተን በሕይወቴ አስቀድማለሁ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon