የግልህ አድርገው

የግልህ አድርገው

«… እኔ ያዘዝኋችሁን ሁሉ ብታደርጉ እናንተ ወዳጆቼ ናችሁ» (ዮሐ.15፡14)።

በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ኢየሱስ ከታዘዝነው የእርሱ ወዳጅ እንደምንሆን ተናገረ። በቀጣዩ የመጽሐፍ ቅዱስ ጥቅስ እርሱ ከዚህ በኋላ ከእንግዲህ ባሪያዎች ብሎ እንደማይጠራቸው ተናገረ፣ ነገር ግን የእርሱ ወዳጆች ናችሁ ብሎ ተናገረ። በግልጥነት ከእርሱ ጋር የግል ህብረት እንዲኖረን ይፈልጋልና እርሱ ከእርሱ ጋር የግል ህይወት እንዲኖረን ይፈልጋል። እርሱ በእኛ ውስጥ ይኖራል በሚለው እውነት ይህንን እውነት ያረጋግጣል። አንድ ሰው በሌላው ሰው ህይወት ውስጥ መኖር የበለጠ አንድ ሰው አንድን ሰው የግሉ ለማድረግ ምን ያህል የበለጠ የግሉ ማደረግ ይችላል።

እግዚአብሔር ከእኛ ርቆ፣ እንደሙያ ዓይነት፣ የባለሙያ ዓይነት ግንኙነት ከእኛ ጋር ህብረት የሚደርግ ከሆነ እርሱ ከእኛ ርቆ ይኖር ነበር። እንዲህ ከሆነ አልፎ አልፎ ይጎበኘን ነበር። እናም እርሱ በእርግጠኝነት ቋሚ መኖሪያ ከእኛ ጋር በተመሳሳይ ሁኔታ ለማድረግ አይመጣም ነበር። ኢየሱስ በመስቀል ላይ በሞተ ጊዜ እርሱ ከኃያሉ እግዚአብሔር ጋር የግል ህብረት ለማድረግ እንድንችል መንገድ ከፈተልን። ይህ ምንኛ የማስደንቅ ሀሳብ ነው። አሁን ስለዚህ አስብ እግዚአብሔር የእኛ የግል ወዳጅ ነው።

እኛ አንድ ሰው ጠቃሚነቱን ካወቅን፣ ለእርሱ አንድ ነገር ለማለት ዕድል ለማግኘት እንወዳለን « ኦው፣ አዎን ያ ሰው የእኔ የግሌ ወዳጅ ነው። ወደ ቤቱ ሁልጊዜ እሄዳለሁ። ብዙውን ጊዜ ከእርሱ ጋር እንጎበኛኛለን» እኛ የእኛን ከእርሱ ጋር ህብረት ለማድረግ ድርሻችንን ከፈጸምን ለእግዚአብሔርም እንዲሁ ተመሳሳይ ነገር ማለት እንችላለን፣ የእርሱን ድምጽ ለመስማትና እርሱ የሚለንን ለመታዘዝ እናም ሁልጊዜ በህልውናው ውስጥ ለመቆየት እንችላለን።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ከእግዚአብሔር ጋር የግል ህብረት ማድረግ ትችላለህ፣ እርሱ ወዳጅህ ነውና።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon