ይቅርታን ማድረግ በጣም ወሳኝ ነገር ነዉ

ይቅርታን ማድረግ በጣም ወሳኝ ነገር ነዉ

ለጸሎትምበቆማችሁጊዜ፥በሰማያትያለውአባታችሁደግሞኃጢአታችሁንይቅርእንዲላችሁ፥በማንምላ ይአንዳችቢኖርባችሁይቅርበሉት።(ማርቆስ 11:25)

የእግዚአብሔርን ድምጽ ለመስማት ከፈለግን፣ በፊቱም ለመቅረብ በቀላሉ በንጹህ ልብ መቅረብ ይኖርብናል፤ በፊቱ ንጹሃን ሆነን ለመቅረብ ደግሞ የበደሉንን ወይም የንዴት ስሜት ዉስጥ ያስገቡንን ሰዎች ይቅር ስንል ነዉ፡፡ የቅር ማለት እንደምናወራዉ ቀላል ነገር አይደለም፣ ዛሬ በምናየዉ ቃል መሰረት፣ ዉጤታማ ለሆነ ጸሎት አስቀድመን ማድረግ ያለብንን ነገር ነዉ፡፡

የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ስለይቅርታ ትምህርት አዲስ ባይሆኑም እንኳ፣ ይቅር ማለት ግን ከብዷቸዉ ነበር፡፡ ጴጥሮስም አንድ ቀን እንደዚህ ብሎ ጠየቀ፣ “በዚያንጊዜጴጥሮስወደእርሱቀርቦ።ጌታሆይ፥ወንድሜቢበድለኝስንትጊዜልተውለት? እስከሰባትጊዜን?”አለው። (ማቴ 18:21) ፡፡ ኢየሱስም አዉቆ እንደዚህ አለዉ፡ “እስከሰባጊዜሰባት፡፡” “ሰባት” ቁጥር የፍጹምነት አመልካች ነዉ፣ ስለዚህ ኢየሱስይላቸዉ የነበረዉ “ለይቅርታ ገደብ አታኑሩ ፤ የቅርታ ማድረግን አታቁሙ፡፡”

ይቅርታን ስናደርግ፣ ክርስቶስን እየመሰልን እንሄዳለን፤ እግዚአብሔር የሚያደርገዉን ነገር አድራጊዎች እንሆናለን፡፡ ይቅርታን ማድረግ የተገለጠ ምህረት ነዉ፤ ይህም በተግባር የሚገለጥ የፍቅር ስራእንጂ በፍቅር ላይ የተመሰረተ ተግባር አይደልም፣ ነገር ግን ፍቅር በዉሳኔ ላይ የተመሰረተ ነዉ፣ አዉቀን እግዚአብሔርን ለመታዘዝ ለማድረግ ሆን ብለን ምናደርገዉ ነገር ነዉ፡፡ ይቅርታን ማድረግ ከፍተኛዉ የፍቅር ጥግ እንደ ሆነ አምናለሁ፡፡ ይቅርታን ማድረግና ፍቅር የማይነጣጠሉና አብረዉ የሚሄዱ እግዚአብሔርንም ከፍ ከፍ የሚያደርጉና የሚያስከብሩ፣

ከሱ ጋር የሚያስማሙን፣ ድምጹን የምንሰማበትን ቃሉን እንድንታዘዝ የሚያደርገን ነዉ፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ ሁል ጊዜ ወዲያዉኑ በቶሎ፣ ፍጹም በሆነ መንገድ ይቅርታ ማድረግህን እርግጠኛ ሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon