ይቅር ለማለት መወሰን

ይቅር ለማለት መወሰን

እውነት እላችኋለሁ፤ማንም ይሄን ተራራ፣ ‘ተነቅለህ ወደ ባህር ተወርወር’ ቢለውና ይህንንም በልቡ ሳይጠራጠር ቢያምን ይሆንለታል፡፡ – ማር 11፡25

የሆነ ሰው ሲጎዳን ምላሽ የምንሰጥበት መንገድ ልክ እንደሰረቀን አይነት ነው፡፡እዳችን እንዳለባቸው ነው የሚሰማን እግዚአብሔር ግን እንድንተው ይፈልጋል፡፡

ይቅር ማለትን እምቢ ካልን የምንፈልገውን ለመቀበል ተስፋችን ምንድነው? እግዚአብሔር በቃሉ ተስፋ የገባልንን ነገሮች ለመቀበል ምንም ያህል ከባድ ቢሆንም መታዘዝ አለብን፡፡ይቅር ማለት አለብን፡፡

በይቅርታ ዙሪያ ሰይጣን ለረጅም ጊዜ የሚጠቀምበት ማታለያ ስሜታችን ካልተቀየረ ይቅር አላልንም ብሎ ማለት ነው፡፡አንድን ሰው ይቅር ለማለት ስትወስኑ ሰይጣን ተመሳሳይ ስሜት ውስጥ ስለሆናችሁ ይቅር አላላችሁም ብሎ እንዲያሳምናችሁ አትፍቀዱለት፡፡

ምንም የተለየ ስሜት ሳይሰማችሁ ይቅር በማለት ትክክለኛውን ውሳኔ መወሰን ትችላላችሁ፡፡እዚህ ጋር ነው እምነት የሚገባው፡፡እናንተ የእናንተን ድርሻ ጨርሳችኋል አሁን እግዚአብሔርን መጠበቅ ነው፡፡እርሱ የእራሱን ሚና በመወጣት ስሜቶቻችሁን ይፈውሳል፣ሙሉ ያደርጋችኋል እናም ለጎዳችሁ ሰው ያላችሁን ስሜት ይለውጠዋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ የጎዱኝን ይቅር ማለትን እመርጣለሁ፡፡ካለባቸው እዳ በኢየሱስ ስም እፈታቸዋለሁ፡፡ልቤን ፈውሰህ ሙሉ አድርገኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon