ጠላቶቻችሁን ነጻ ማውጣት

ጠላቶቻችሁን ነጻ ማውጣት

የሚያሳድዷችሁን መርቁ፤መርቁ እንጂ አትርገሙ፡፡ – ሮሜ 12፡14

ስላለፉት ጉዳቶቻችን ስናስብ ይቅር ማለት ከባድ በሆነበት ሰአት እንኳን ትክክለኛው ነገር እንደሆነ እናውቃለን፡፡ቢሆንም ግን እግዚአብሔር እንድንወስደው የሚፈልገውን ቀጣዩን እርምጃ የምንወስደው ግን ከስንት አንዴ ጥቂቶቻችን ነን፡፡

በጣም የተለመደው ስህተት ማድረግ ያለብን ብቸኛው ነገር ይቅር ለማለት መወሰን እና ስራችን አልቋል ብሎ ማሰብ ነው፡፡ነገር ግን ኢየሱስ የሚያሳድዷችሁን መርቁ ስለሚረግሟችሁ ሰዎች ደስታ ጸልዩ እና በሚበድሏችሁ (ለሚነቅፏችሁ፣ለሚዘልፏችሁ፣ለሚያንኳስሷችሁ እና በሀይል ያለአግባብ በሚጠቀሙባችሁ) ላይ የእግዚአብሔርን በረከት(ሞገስ) ጥሩ ብሏል (ሉቃ 6፡28)፡፡በተጨማሪም ሮሜ 12፡14 የሚያሳድዱንን እና በጭካኔ የሚይዙንን ሰዎች መባረክ እንዳለብን ይናገራል፡፡

ጠላቶቻችንን ንቁ በሆነ መንገድ መባረክ አለብን፡፡እግዚአብሔር ለማይገባቸው ሰዎች ምህረትን እንድናደርግ ነው የጠራን፡፡ለምን?

ይቅር ስትሉ እግዚአብሔር እናንተን ለመፈወስ በር ይከፈትለታል እውነቱን ለመነጋገር ግን ላሳዘናችሁ ሰው ብዙም ጥቅም የለውም፡፡እናንተ ግን ስትባርኳቸው ንስሀ ገብተው እርሱ የሚሰጠውን እውነተኛ ነጻነት ይለማመዱ ዘንድ እግዚአብሔር እውነትን ወደ እነርሱ እንዲያመጣ ጠይቁላቸው፡፡ይቅርታ ነጻ ያወጣችኋል…ጠላቶቻችሁን መባረክ እነርሱን ነጻ ያወጣቸዋል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በይቅርታ እንድራመድ ስለረዳኸኝ አመሰግንሀለሁ፡፡ነገር ግን እዚህ ላይ ማቆም አልፈልግም፡፡የጎዱኝን ሰዎች እንድትባርካቸው እጸልያለሁ፡፡ልክ ለእኔ ፈውስን ባመጣህበት መንገድ ለእነርሱም መልካምነትህን ይለማመዱ እና በፍቅርህ ይጓዙ ዘንድ ፈውስን አምጣላቸው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon