ጭምብሉን አዉልቀዉ

ጭምብሉን አዉልቀዉ

እኛም ሁላችን በመጋረጃ በማይከደን ፊት የጌታን ክብር እንደ መስተዋት እያብለጨለጭን መንፈስ ከሚሆን ጌታ እንደሚደረግ ያን መልክ እንመስል ዘንድ ከክብር ወደ ክብር እንለወጣለን። – 2 ቆሮ 3:18

ዙ ጊዜ በዉጪ ገጽታችን የምናሳየዉ ነገር ከዉስጠኛዉ ጋር የተለየ ነዉ፤ ይህንን የምናደርገዉ ድካሞችና ስህተቶች ስላሉብን፣ እኛ ያሰብነዉ ነገር ተቀባይነታችንን ያሳንሳል ብለን ስናስብ ነዉ ከሌሎች ሰዎች እዉነተኛ ማንነታችን የምንደብቀው፡፡ ስለዚህ ጭንብል እንለብሳለን፡፡

ጭንብል የመልበስ አደጋዉ እኛን አዛብቶ መወከሉ/ማሳየቱ ነዉ፡፡ ሌሎች ሰዎች የሚያዩት ዉሸት ነዉ፤ ያ እኛ አይደለንም ወይም እኛ የተወለድንበት ዓላማ አይደለም፡፡ ዉጫዊ ገጽታችንን መቀየር እንችል ይሆናል ነገር ግን የዉስጥ ማንነታችንነ መቀየር አንችልም እግዚአብሔር ብቻ ነዉ ልባችንን መለወጥ የሚችለው፡፡

እግዚአብሔር እንዲሁ አሁን እንዳለን እንደሚወደንና ፍቅሩንም መቼም እንማይቀንስ ልናስታዉል ያስፈልጋል፡፡

በተጨማሪ ሌላ የበለጠ መልካም ዜና አለ 2 ቆሮ 3፡18 የሚናገረዉ እግዚአብሔር እየቀየረን እንደሆነና እርሱን እንድንመስል ከህይወታችን እንከኖችን እያስወገደ እንደሆነ ነዉ፡፡

ጭንብልህን እንዲያወልቀዉ ወደ እርሱ ዘወር በል፤ እናንተ ታገኙታላችሁ እኔ እንዳግኘሁት፤ አንተም ቀስ በቀስ ጌታን ወደ መምሰል እየተለወጣችሁ እንደሆነ ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ተቀባይነት ለማግኘትና ብቁ ለመምሰል ስል ዘወትር ጭንብል እንደማጠልቅ አስተዉዬአለሁ፡፡ ዛሬ ተቀባይነትን በአንተ ለማግኘት ምርጫ አድርጌአለሁ፡፡ በፍቅርህ እንደሞላኸኝ አንተን ወደ መምሰል መቀየርህን ቀጥል፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon