ጭንቀት ድብቅ ራስ ወዳድነት ነዉ

ጭንቀት ድብቅ ራስ ወዳድነት ነዉ

ነገር ግን የሚጠራጠር ሰዉ ቢበላ በእምነት ስላልሆነ፣ ተፈርዶበታል፤ በእምነት ያልተደረገ ሁሉ ኀጢአት ነዉና፡፡ – ሮሜ 14:23

ዙ ጊዜ ሰዎች እንዴት አፍራሽ እንደሆነ ልብ ሳይሉ ለጭንቀት ይጋለጣሉ፡፡ ወደ ሥሩ የሄድህ እንደሆነ ጭንቀት ኀጢአት ነዉ፡፡ ጭንቀት በፍጹም ከእምነት አይመጣም፡፡ ሮሜ 14፥23 ያስቀመጠልን በእምነት ያልተደረገ ሁሉ ኀጢአት እንደሆነ ነዉ፡፡

አብዛኛዉን ጊዜ ጭንቀት የሚመሰረተዉ በተለይም በአንድ ኀጢአት ላይ ነዉ፤ በራስ ወዳድነት፡፡ ዘወትር ስንጨነቅ የምናስበዉ እንዴት ራስ ወዳድ ፍላጎቶቻችን እንዳልተሟሉ ነዉ፡፡ ራስ ወዳድ ፍላጎቶችህ በበዙ ቁጥር ሲጨምሩ ፤ የበለጠ ስለ ነገሮች መጨነቅና ሕይወትህም የበለጠ መመሰቃቀል ይጀምራል፡፡

እግዚአብሔር እርሱን በማገልገል ላይ እንድናተኩር ነዉ የሚፈልገዉ፡፡ የእግዚአብሔር ፈቃድ ከስጋትና ከጭንቀት ነጻ የሆነ ሕይወት እንኖር ዘንድ ነዉ፡፡ እርሱ ባልተከፋፈለ ልብ እንድናገለግለዉ ይፈልጋል (1ኛ ቆሮ 7፥34ን ተመልከት)፡፡ የዚህ ዓለም ጭንቀቶች እርሱ ለህይወታችን ካለዉ ዓላማ ይመልሱን ዘንድ አንፍቀድላቸዉ፡፡

ራስ ወዳድ ፍላጎቶችህን እንድታስተዉልና እንድታስወግድ ይረዳህ ዘንድ ወደ እግዚአብሔር ጸልይ፡፡ ይህ ህይወትህን ቀላል ያደርግልሃል ጭንቀቶችህንም ማሸነፍ እንድትችል ይረዳሃል፡፡ ከዚያም እግዚአብሔር ለሕይወትህ ያለዉን ታላቅ ዓለማ በሙሉ ልብ መከተል ትችላለህ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

አባት ሆይ! መጨነቅ ኀጢአት እንደሆነ ስላሳየኸኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ራስ ወዳድ ፍላጎቶቼን እንዳስወግድና ለህይወቴ ያለህን ግብ መከተል እንድችል እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon