እንደምወዳቸው ንገሯቸው

እግዚአብሔር ቤተሰብ ስለሚፈልግ ልጆቹ እንድንሆን አደረገን፡፡ እግዚአብሔር እንደ ልጆቹ እንጂ ሕፃናት እንድንሆን አይሻም፡፡ ነገር ግን እርሱ እንድንሆን የሚፈልገው እንደ ልጆቹ ነው፡፡ በእርሱ ላይ እንድንደገፍ፣ እንድንመረኮዝና እንድናርፍ ይፈልጋል ደግሞም እንድንወደውና እርሱም እንዲወደን ይፈልጋል አንዳች የሚያስፈልገን ነገር ሲኖር በእርሱ እንድነታመንና ወደ እርሱም እንድንመጣ ይፈልጋል፡፡ እርሱ ከአንተ ጋር ኅብረት ለመመስረት ይፈልጋል፡፡ ብዙዎቻችን ዮሐንስ 3÷16 የምንመለከተው ሰፋ ባለ ትርጉሙ ነው፡፡“እርግጥ ነው ኢየሱስ ለዓለሙ ሁሉ እንደሞተ አውቃለሁ” እንላለን፤ ነገር ግን ኢየሱስ ለመላው ሕዝብ ብቻ አይደለም፤ እርሱ ለእያንዳንዳችን ሞቷል፤ እርሱ ለአንተም ሞቷል!

አውርድ
እንደምወዳቸው ንገሯቸው
Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon