እግዚአብሔር ይወዶታል! ከእርሶ ጋር የቅርብ ወዳጅነትን ሊመሰርት ይፈልጋል፡፡ እየሱስ ክርስቶስን የሕይወቶ አዳኝ አድርገው ካልተቀበሉ÷ አሁን ሊቀበሉት ይችላሉ፡፡ ልብዎትን ይክፈቱና ይህንን ፀሎት ይፀልዩ….
“አባት ሆይ! በአንተ ላይ በደልን እንደሰራሁ አውቃለሁ፡፡ እባክህ ይቅር በለኝ፡፡ ኃጢአቴን አንጽተህ እጠበኝ፡፡ በልጅህ በእየሱስ ለመታመን ቃል እገባለሁ፡፡ ልጅህ እንደሞተልኝ አምናለሁ፣ በመስቀል ላይ ስለ እኔ ሲሞት ኃጢአቴን የራሱ አድርጎ ወስዶልኛል፡፡ ከሙታንም እንደተነሣ አምናለሁ:: አሁን በዚህ ሰዓት ህይወቴን ለእርሱ አስገዛለሁ::
“አባት ሆይ ስለ ይቅርታና የዘላለም ሕይወት ስጦታህ አመሰግንኃለሁ:: ለአንተ ብቻ እንድኖር እባክህ እርዳኝ፡፡ በእየሱስ ስም አሜን !”፡፡
ከልብዎት እንደፀለዩ ሁሉ÷ እግዚአብሔር ተቀብሎዎታል÷ ከኃጢአቶትም አንጽቶታል÷ ከመንፈሳዊ ሞት እስራትም ፈጽሞ ነፃ ወጥተዋል፡፡ እነዚህን የመጽሐፍ ቅዱስ ምንባቦች እያነበቡ ከእግዚአብሔር ጋር በሚያደርጉት የአዲስ ሕይወት ጉዞ ለልቦ እንዲናገርዎት ሁልጊዜ ይፀልዩ፡፡
ዮሐንስ 3፡16 1ቆሮንጦስ 15፡ 3-4
ኤፌሶን 1፡4 ኤፌሶን 2፡ 8-9
1ኛ ዮሐንስ 1፡9 1ኛ ዮሐንስ 4፡ 14-15
1ኛ ዮሐንስ 5፡1 1ኛ ዮሐንስ 5፡ 12-13
መጽሐፍ ቅዱስን መሠረት ያደረገ ቤተክርስቲያን እንዲያገኙና ከክርስቶስ ጋር ባለዎት ሕብረት እንዲያድጉና እንዲበረታቱ ይፀልዩ:: እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከእርስዎ ጋር ነው፡፡ ቀስ በቀስ በየእለቱ ይመራዎታል፡፡ ለእርስዎ ባዘጋጀው የተትረፈረፈ ሂወት እንዴት መኖር እንዳለብዎት ያሳይዎታል፡፡
እህታችን ጆይስ እግዚአብሔር በምድራችን ላይ በሙላት ካሰነሳቸው የመጽሐፍ ቅዱስ አስተማሪዎች መካከል አንደኛዋ ናት፡፡ ኒዎርክ ታይምስ መጽሔት በአንድ ወቅት መጽሐፎቻቸው ከሚነበቡላቸው ሠዎች መካከል በግምባር ቀደምትነት አስቀጧታል::
ይህቺ የእግዚአብሔር ሴት በአለም አደባባይ ላይ በሥነ ጽሑፍ ትሩፋቶቿ አንቱታን እንድታገኝ ያደረጓት መጽሐፍት መካከል እንሆ ጥቂቶቹን፡- ህይወትን ቀሊል የሚያደርጉ 100 መንገዶች፣
ተስፋ አትቁረጥ፣ ከአህይምሮ ውጊያ ጋር ትንታኔ የሚሰጡ በርካታ የቤተሰብ መጽሐፍት እንዲሁም ፈረንካና በማንኛውም ደቂቃ የተባለሁለት የክርስቲያን ልብወለድ መጽሐፍት የሆኑትን ለአንባቢያን አቅርባለች::
ጆይስ ማየር ከእነዚህ የሥነ ጽሑፍ ትሩፋቶች በተጨማሪ በሺህ የሚቆጠሩ በርካታ የድምጽና የምስል ቃለ እግዚአብሔር አስተምሮቶቿንም ለመላው አለም እንዳቀረበች ይታወሳል፡፡ ጆይስ ማየር
በመላው አለም በሚሊዮኖች ዘንድ የሚታወቅ የራዲዮና የቴሌቪዥን ፕሮግራም አላት፡፡ ይህ ፕሮግራም በየዕለት ህይወታችን እንደሰት የሚል ፕሮግራም ነው፤ በፕሮግራሙ አማካኝነትም ሠዎች በመላው አለም ህይወታችን በደስታ ህይወት ውስጥ እንዲገቡ ምክንያት ሆኗል፡፡
በዚህ ርእሰ ጉዳይና በሌሎች ርእሶች እህታችን ጆይስ በመላው አለም በሚደረጉ የጀማ ወንጌሎችና ሴሚናሮች ላይ እየተገኘች ታገለግላለች:: በአሁኑ ሠዓት እህታችን ጆይስ ከውድ ባለቤቷ ከዴቭ ጋር በቁጥር አራት ከሆኑት ውድ ለጆቻቸው ጋር አሜሪካ ምድር በሚዚዮሪ ግዛት በቅዱስ ሉይስ ከተማ ይኖራሉ፡፡