ተስፋ በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ

ምናልባት የወደፊት ተስፋን የሚያጨልም አሳዛኝ ሁኔታ ውስጥ እያለፍክ ሊሆን ይችላል፣ ወደፊት ለመሄድ የትኛውን መለየትና መምረጥ እንዳለብህ እርግጠኛ ላትሆን ትችላልህ ምናልባት ደግሞ የጤና ችግር ገጥሞህ ሐኪም ቤት የምትኬድበትን አጥተህ ሊሆን ይችላል፡፡ ብዙ ሰዎች የሚቀጥለው ምግባቸውን ከየት እንደሚያገኙ እርግጠኛ ባልሆኑበት የዕለት ተዕለት ሕይወታቸውን እንደሚገፉ አውቃለሁ፡፡

በማይመስል አስቸጋሪ ጉዳይ ውስጥ ስናልፍ ጉዳዩን በመተው እንድናቋርጥ እንፈተናለን፡፡ ይሁን እንጂ አንዱና ትልቁ ነገር ማድረግ የምንችለው እምነታችንን በእግዚአብሔር ላይ በማድረግ በሙሉ ተስፋ በእርሱ መጽናት ነው፡፡ ይሁን እንጂ በእርግጥ ተስፋ ራሱ ምንድ ነው?

ተስፋ የምንጠብቀው አንድ መልካም ነገር እንደሚሆን አርግጠኛ መሆን ነው፡፡ እርሱም በቀጥታ ከእምነታችንና ከምናምንበት ነገር ጋር የተቆራኘና የተዛመደ ነው፡፡ በተስፋ ስንሞላ ሕይወታችን በሰላምና በደስታ ይጥለቀለቃል፡፡

ጠላታችን ተስፋ ቢሶች እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ እርሱ ሁሉ ነገር እንዲጠፋና ምንም ነገር ወደ ጥሩ ነገርና ወደ ትክክለኛ መንገድ እንደማይመጣ ሊያሳምነን ይጥራል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር በተስፋ ተሞለተን ከእርሱ ትልቅ ነገርን እንድንጠባበቅና እንድናምን ይፈልጋል፡፡ በእርግጥ መጽሐፍ ቅዱስ “እርሱ የተስፋ አምላክ ነው፡፡” የአዲስ ነገር ጀማሪ ነው ይላል፡፡ (ሮሜ 15፡13 ተመልከት)

Straight Talk on Discouragement AMHARIC

ስማኝ ተስፋ መቁረጥ

ሰይጣን በረቀቀው መንገዱ ሁለንተናችንን ማለትም ሰውነታችንና ነፍሳችንን ከመጨቆን ወደ ኋላ አይልም፡፡
እንደምወዳቸው ንገሯቸው

እንደምወዳቸው ንገሯቸው

እግዚአብሔር ይወድሃል!
ለምን ጌታ ሆይ?

ለምን ጌታ ሆይ?

ግራ ተጋብታችኋል? አንድ እንግዳ ነገር፣ ፈጽሞ ሊገባችሁ ያልቻለ ጉዳይ በህይወታችሁ ሳትፈልጉት እየሆነባችሁ ይሆን?
Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon