አትፍራ

አትፍራ

እኔ አምላክህ እግዚአብሔር አትፍራ እረዳሃለሁ ብዬ ቀኝህን እይዛለሁና፡፡ ኢሣ 41÷13

አንዳንድ ጊዜ እኛ መንፈስ ቅዱስ መከተል ስንፈልግ ተቃውሞ ይገጥመናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ይህ ተቃውሞ ደግሞ የሚመጣው በፍርሃት መልክ ታላቅ ተፈጥሮአዊ አደጋ ፍርሃት ወይም አስጨናቂ በሽታ እንዲሁም ደግሞ እንደመቅሰፍት የመሳሴሉ ናቸው፡፡ ነገር ግን እረፍት ማጣትና ለተለመዱ ጉዳዮችና ተራ ነገሮች መቅበዝበዝ ፡ ሰይጣን ሌላው ቀርቶ በድፍረት እንዳንፀልይ እንኳ ሊያደርግ ይሞክራል፡፡ ሰይጣን እኛ እግዚአብሔርን በእምነት ሳይሆን በፍርሃት እንድንቀርበው ይፈልጋል፡፡

ብዙ ሰዎች እያንዳንዱን ቀን ቋሚ በሆኑ ጥቃቅንና ወቅታዊ ሁኔታዎች ሥር በመመላለስ ይኖራል፡፡ በሕይወታቸው እንዲህ ዓይነት ግምትና አስተያየት ይሰጣሉ፡፡ ይሄ የትራፊክ መጨናነቅ በሥራ ቦታዬ በጊዜ እንዳልደርስ ያደርገኛል ብዬ እፈራለሁ፡፡ ጥብሱ ይቃጠልብኛል ብዬ እፈራለሁ፣ ቅዳሜ በሚኖረኝ የእግር ኳስ ጨዋታ ወቅት ዝናብ ይዘንብ ይሆን ብዬ እፈራለሁ፡፡ እነዚህ የየእለት ፍርሃቶች እግዚአብሔርን ከማዳመጥ በመጋረድ ሰዎች በሁኔታዎችና በችግሮቻችን ላይ እንዲያተኩሩ ያደርጋሉ፡፡ በተለመደውና በሚቀጥለው ጥቃቅን ችግሮች ጠላት ተጠቅሞ ሕይወታችንን እንዲያጠቃ ከማድረግ ይልቅ ወደ እግዚብሔር መፀለይና እርሱን መታመን ይሻለኛል፡፡

የሕይወቴ መመሪያ ‹‹ስለሁሉም ነገር ፀልይ ነገር ግን አትፍራ›› የሚል ነው፡፡ ለእግዚአብሔር የመናገርና የማዳመጥ የሕይወት ዘይቤአችንን እያደገ ሲመጣ በከፍተኛ ደረጃ ጥቃቅን ፍርሃታችንና ልማዶችን እንዲሁም የፀሎት የመግዳዴሩትን መንገድን አጥብቀን መቋቋም እንጀምራለን፡፡ መንፈስ ቅዱስም ይህንን ይሬዳናል ፡ መጥፎ ከሆነ ልምምድ ወጥተን ወደ ጥሩ ልምምድና ባሕሪ በመግባት በቀኑ መጠየቅ አለብን፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን እንዲመራን በፈቀድንለትና በጣም ቀላልና ልክ አየርን እንደመተንፈስ የተለመደ የሕይወት መንገድ ይሆንልናል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ስለሁሉ ነገር ፀልይ ምንም ነገር አትፍራ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon