ሁሉም ቀን አዲስ ቀን ነው

ሁሉም ቀን አዲስ ቀን ነው

እግዚአብሔር የሠራት ቀን ይህች ናት፤በእርሷ ሐሤት እናድርግ፤ ደስም ይበለን። – መዝሙ 118፡24

እግዚያብሔር በእያንዳንዱ ቀናችን መካከል ደስተኞች እንድንሆን ይሻል ምንም እንኳ አስቸጋሪ ወቅቶች ቢኖሩብንም ዓላማው ይህ ነው፡፡ በህይወቴ ውስጥ እያንዳንዷ ከባድ የነበረች ጊዜ ነበርች እኔና ባለቤቴ ዴቭ ያሉብንን የቤትና መሰል ክፍያዎች እንዴት እንደምንከፍል ሳስብ፤ አንዳንድ ጊዜ ሁሉም ነገር ከአቅሜ በላይ ይሆንና በአልጋዬ ላይ ተጠቅልዬ እተኛለሁ፡፡

በጭንቀት ከመሸፈኔ ብዛት የእግዚያብሔርን አላማ ረሳሁ ፣ እሱም እግዚያብሔር አዲስ ቀንን ፈጥሯል ፤ የፈጠረውም እኔ ደስተኛ እንድሆንበት መሆኑን ነው፡፡ እያንዳንዱ ቀን እናንተ የምታዝኑበትና ምቾት እንዳይሰማችሁ የሚሆንበት አጋጣሚዎች ሊኖሩበት ይችላል ነገርግን ሰላምን መመረጥና ችግራችሁን መቆጣጠር ትችላላችሁ፡፡

አእምሮአችንን ከችግራችን ላይ አንስተን ትኩረታችንን እግዚአብሄር ላይ እና ሌሎች ሰዎችን መውደድ ላይ ማድረግ ስንጀመር ፤ እግዚያብሔርን ደስ የሚያሰኝ ባህሪ እየያዝን እና እያንዳንዱ ቀናችንን ከእግዚአብሄር የተሰጠን ስጦታ አድርገን ማየት እንጀምራለን።


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ስለሰጠኽኝ አዳዲስ ቀናት አመሰግንሃለሁ ከአሁን በኋላ ስለድካሜ ከማሰብ በአንተ ላይ በመደገፍ በአንተ ደስ እሰኛለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon