ሁልጊዜ ከአንተ ጋር ነው

ጻድቃንም በእውነት ስምህን ያመስግናሉ፤ ቀኖችም በፊጽህ ይኖራሉ፡፡ መዝ 140፡13

የመንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ መኖር የሚያረጋግጠው የእርሱ ሁልጊዜ ከእኛ ጋር መሆንና እኛ ስንጠይቀው ሊናገረንና ሊረዳን እንደሆነ ማረጋገጫ ነው፡፡ በመንፈሣዊ ሕይወት ባደግን ቁጥር የተለያዩ ፈተናዎች ውስጥ እናልፋለን፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የሰጠን ለመቋቋም እንድንችልና ትክክለኛ ምርጫ እንድናደርግና ከመሳሳት እንድንጠበቅ ነው፡፡

ማንም የሰው ልጅ ፍጹም ስላልሆነ ስህተት ብንሰራም ነገር ግን የእግዚአብሔር ምህረት ሁሌ በኢየሱስ ክርስቶስ ከእኛ ጋር ነው፡፡ እርሱም ይህንን ምህረት ለመቀበል እንድንችል ያበረታታንና ወደ ሬት ጉዞአችንን ለመቀጠል ያስችለናል፡፡ እንዲሁም ልባችንን በሠላም በነፃነት ሆነን የእግዚአብሔርን ድምፅ በማጣራት ለመስማት ያስችለናል፡፡

እያንዳንዱን ስህተታችንን ተከታትለን እራሳችንን እየኮነንና የተሸነፍናትን ስሜት ስናስተናግድ እራሳችንን እናደክማለን፡፡ የእኛን ኃይል በመጥፎ ማንነታችን ከመሙላት ይልቅ ያንን ኃይላችንን ልባችን ከዚያ ወደ ተሻለ ብርታትና ጥልቅ ሕብረት ገብቶ የእግዚአብሔርን ድምፅ በመስማት ላይ እንዲያተኩር ብናደርግ ውጤታማ ያደርገናል፡፡

የእርሱ መገኘትና የእርሱ ምህረት ሁልጊዜ በመንፈስ ቅዱስ በኩል ለእኛ ቀርበዋል፡፡ ዛሬ እግዚአብሔርን እንድትፈልግና የእርሱን ፍቅርና ምህረት እንድትቀበል አበረታታሃለሁ፡፡ የእርሱ እጆች ተዘርግተው ጊዜ ከአንተ ጋር ለመውሰድ እየጠበቀ ነው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- መንፈስ ቅዱስ ለአንተ ቅርብ እንደሆነ አስተውል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon