‹‹ … ለምኑ፥ ይሰጣችሁማል፤ ፈልጉ፥ ታገኙማላችሁ፤ መዝጊያን አንኳኩ፥ ይከፈትላችሁማል። የሚለምነው ሁሉ ይቀበላልና፥ የሚፈልገውም ያገኛል፥ መዝጊያንም ለሚያንኳኳ ይከፈትለታል›› (ማቴ.7፡7 -8) ።
ኢየሱስ እንድለምን፣ እንድንፈልግና እንድናኳኳ ተናገረ፡፡ ማንም ሰው ካላንኳኳ የሚከፈት በር የለም፤ ማንም ሰው ካልፈለገ አያገኝም፤ ማንም ሰው ካልለመነ አይቀበልም፡፡ ለመቀበል የምንፈልግ ከሆነ መለመን የግድ ያስፈለልገናል፡፡ምክንያቱም የእኛ ልመና እጅግ ጠቃሚ ነገር ነው፡፡ እኛ እግዚአብሔርን እንደለመነው በእርግጥ ልመናችን ለምስጋናችንና ለውዳሴአችን ክብደትን የሚሰጠው እንዳይሆን እርግጠኛ መሆን አለብን፡፡ ምክንያቱም ከምናመሰግነው በላይ መለመን የለብንም፡፡ በፊል 4፡6 ላይ ያለውን የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል ማስታወስ ያስፈልገናል፡፡ ‹‹ … ጌታ ቅርብ ነው። በነገር ሁሉ በጸሎትና በምልጃ ከምስጋና ጋር በእግዚአብሔር ዘንድ ልመናችሁን አስታውቁ እንጂ በአንዳች አትጨነቁ››። ምስጋናችንና ውዳሴአችን ወደ እግዚአብሔር ከምናቀርበው ልመናችን ጋር ሚዛናዊ ሲሆን እጅግ የሚየያስደንቅና የሚያስገርም ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ስለአንድ ነገር መጠየቅ /መለመን/ አስደናቂ ነው፡፡ እግዚአብሔርን ለጸለይከው ልመና እመን፣ ከዚም በህይወታችን ውስጥ መልሱን ሲያመጣው አስተውለህ ተጠባበቀው፡፡በልባችን የጸለይነውን ጸሎት እንደተቀበልንልናወቅ እንችላለን፤ እናም በድጋሚ እግዚአብሔርን ማሳሰብ ፈጽሞ አያስፈልገንም ወይም ምናልባት በጸሎት መጽናት እንዳለብን ይሰማን ይሆናል፤ በሌላ መንገድ እግዚአብሔር በራሱ ጥበብና በራሱ ጊዜና በራሱ መንገድ መልስ ሊሰጠን እንደሚወድ፤ ለጸሎታችን መልስ እንደሚሰጥ እንደሚወድ እርግጠኛ መሆን እንችላለን፡፡ ስለዚህ ለመለመን (ጸሎት)፣ ለመፈለግና ለማንኳኳት ወደ ኋላ አትበል (አትተው)፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ልመናህ ከምስጋናህና ከውዳሴህ እንዲበልጥ መፍቀድ የለብህም፡፡