ለስኬት ቁልፉ

ለስኬት ቁልፉ

ስለዚህ የሠራዊት ጌታ እግዚአብሔር እንዲህ ይላል: – መንገዶቻችሁን አስተውሉ ወደ እናንተም በመጣላችሁ ላይ አተኩሩ። (ሐጌ 1:5)

እግዚአብሔር ለአንተ እና ለእኔ ያቀደው በጣም ትልቅ፣ አስደናቂ፣ የስኬት ሕይወት አለው፣ ነግር ግን ግትር ከሆንን (ዘጸአት 33፡3 ን ተመልከት) ወይም ልበ ደንዳና ከሆንን ያንን ለእኛ ያለውን እናጣለን። ግትርነት እና የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት እና ለመታዘዝ እምቢ ማለት በመንገዶቻችን ላይ እንድንቀመጥ እና እድገት እንዳናሳይ ያደርገናል። በዚህ ሁኔታ ውስጥ ራሳችንን ስናገኝ ብዙውን ጊዜ ቆም ብለን ችግሩ ምንድነው ብለን እራሳችንን መጠየቅ ያቅተናል።

የዛሬው ክፍል የእግዚአብሔር ሕዝብ ያልረኩበትን ደግሞም ብዙ ችግሮች ያጋጠሙበትን ጊዜ ይናገራል፣ ስለዚህም እግዚአብሔር መንገዶቻቸውን እንዲመረምሩ ነግሯቸዋል። ብዙ ጊዜ ሰዎች በህይወት ሳይሳካላቸው ሲቀር ምክንያቱን ፍለጋ ከራሳቸው በስተቀር ወደትኛውም ቦታ ይመለከታሉ። በሕይወትህ ካልተሳካልህ፣ እግዚአብሔር የብሉይ ኪዳን ሰዎችን እንዲያደርጉ እንዳዘዛቸው አድርግ እና አካኼድህን መርምር”። ስለ “መንገድህ” እንዲነግርህ እግዚአብሔርን ጠይቅ፣ ደግሞም ለሚናገረው ነገር ትኩረት ስጥ። ይህንን ብዙ ጊዜ ማድረግ ነበረብኝ፣ በውጤቱም በአስተሳሰቤ፣ በአላማዬ ወይም በባህሪዬ ላይ ለውጦችን ማድረግ ነበረብኝ።

ከጊዜ በኋላ አካኼዴን ስመረምር ግትር፤ ተቺ፣ ኩራተኛ እና ሌሎችም ብዙ እድገት እንዳላመጣ ያደረጉኝን ስሆን አግኝቼዋለሁ። ነገር ግን እግዚአብሔርን አመሰግናለሁ፣ እርሱ ለውጦኛል! እኔን መለወጡን እንዲቀጥል ደግሞም በፍጹም እንዳያቆም እጸልያለሁ።

እግዚአብሔር እንዲኖረኝ የሚፈልገው ሁሉ እንዲኖረኝ ደግሞም እርሱ እንዲኖረኝ የማይፈልገው ሁሉ እንዳይኖረኝ እፈልጋለሁ። እኔ የእርሱ ነኝ እንተም እንዲሁ። እግዚአብሔር ደስተኛ እና የተባረከ በእርካታ እና በስኬት የተሞላ አስደናቂ ሕይወት እንዲኖርህ ይፈልጋል። አንተም እንደዚህ ዓይነት ሕይወት የማትኖር ከሆነ፣ አካሔድህን ለመመርመር ጊዜ ውሰድ፤ መለወጥ ያለብህን እንዲያሳይህ እግዚአብሔርን ጠይቅ፣ ከዚያም የሚያዝህን አድርግ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ስለራስህ እውቱን ለመጋፈጥ አትፍራ ምክንያቱም ነጻ ያወጣሃልና።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon