ለጋስ እና ደስተኛ ሁን

ለጋስ እና ደስተኛ ሁን

እያንዳንዱ ሰው በቅሬታ ወይም በግዴታ ሳይሆን፣ በልቡ ያሰበውን ያህል ይስጥ፤ ምክንያቱም እግዚአብሔር በደስታ የሚሰጠውን ሰው ይወዳል። – 2 ቆሮ 9፡7

እንደ ክርስቲያን ለጋስ ሕዝብ መሆን ይገባናል ፤ የምንችለውን ነገር በቻልነው አጋጣሚ መለገስ አለብን፡፡ የምንለግሰው የግድ ገንዘብ ብቻ መሆን የለበትም ፤ ለሰዎች እረዳታን ፣ ማበረታቻን ፣ ጊዚያችንን ፣ ክህሎታችን እና ይቅርታን ልናበረክት እንችላለን፡፡ ይህ ማለት ራስ ወዳድነት መንገዳችን ውስጥ ሳይገባብን ማለት ነው፡፡ አንዳድ ሰዎች ካላቸው ነገር ጋር የተጣበቁ እና ባላቸው ነገር ላይ የተንጠላጠሉ በመሆናቸው ያለቸውን ለመስጠት ፍርሃት ይሸብባቸዋል ፤ ሌሎች ደግሞ መስጠት ሳይሆን ልባቸው ነው ቅር ሚለው ፤ መስጠትም ካለባቸው የሚሰጡትን ትዕዛዝ በመሆኑ ብቻ እንጂ ከልግስና ልብ ተነሳስተው አይደለም፡፡ ይሁን እንጂ እግዚአብሔር እንድንሰጥ በሚፈለገው በዚህ አግባብ አይደለም፡፡ በሁለተኛ ቆሮ 9፡7 እግዚአብሔር የሚሰጥ ሰው ያለ ቅሬታ ወይም ግዴታ እንዲያው በደስታ የሚሰጠውን ይወዳል ፡፡ ሕይታችንን ለእግዚአብሔር በመንገዳችን ያለ የእኛ የምንለው ነገር የእርሱ እንጂ የእኛ አይደለም፡፡

እግዚብሔር እንድንለግስ በሚፈልግበት መንገድ ሰጪዎች መሆን ይገባናል፡፡ ዛሬ በደስታ ስጡ፡፡ በደስታ የሚሰጡ ሰዎች ደስተኞ ፣ የተሳካላቸው እና ውጤታማ ሰዎች ናቸው፡፡ እግዚአብሔርንም የሚያስደስት ተግባር ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ በደስታ የሚሰጥ ሰው እንደሆን በልቤ እና በአዕምሮ አሁን እወስናለሁ፡፡ እንዴት አድርጌ በልግስና ላንተ እና ለሰዎች መስጠት እንደምችል አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon