. . . የሚመጣውንም ይነግራችኋል፡፡ ዮሐ 16÷13
እግዚአብሔርን መስማት ከሚጠቅሙን ነገሮች መካከል አንደኛው እግዚአብሔርን ስናደምጥ ሊመጣ ያለውን በማሳወቅ እንድንዘጋጅ ይረዳናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ እግዚአብሔር አባት የሚሰጠውን መልዕክት ለእኛ ይሰጠናል፡፡ መንፈስ ቅዱስ አብዛኛውን ጊዜ ወደፊት ሊሆን ያለውን ይነግረናል፡፡
እግዚአብሔር አስቀድሞ ለሕዝቡ ሊሆን ያለውን ነገር ስለ ጉዳት መረጃ እንዲሰጣቸው ብዙ ምሣሌዎች ከመጽሐፍ ቅዱስ ማግኘት ይችላል፡፡ ለኖህ የጥፋት ውሃ መጥተው በምድር ላይ ያሉትን ሕዝብ ከማጥፋት አስቀድሞ መርከብ እንዲያዘጋጅ ነግሮት ነበር፡፡ (ዘፍ 6÷13-17 ተመልከት)፡፡
ሙሴ ሄዶ የእስራኤልን ሕዝብ እንድለቅ ለፈርኦን እንድናገር ነገር ግን ፈርኦን እሺ ብሎ በቀላሉ እንደማይለቅ አስቀድሞ ነግሮት ነበር (ዘፀ፡7)፡፡ ግልፅ መሆን ያለበት እግዚአብሔር ወደፊት የሚሆነውን እያንዳንዱን ነገር የሚነግረን ሳይሆን ቃሉ እንደሚል ስለአንዳንድ ነገሮች ይነግረናል፡፡
በሕይወቴ አንዳንድ ጊዜ መልካም ነገር ወይም ፈታኝ የሆኑ ነገሮች ሊሆኑ እንዳሉ ይሰማኛል፡፡ የሆነ ፈተና ሊገጥመኝ ሲል ያለፈውን የቀድሞ ተሞክሮ አለኝ፡፡ ያለዕውቀት ወይም መረዳት በመንተራስ በአስቸጋሪ ሁኔታ ውስጥ ይረዳኛል፡፡ የመኪና ሞተር እርስ በርሱ በትክክል ነዳጅ እየተቀባበለ ሲመጣ በሰላም ስለሚናዳ ግጭት ከመቅረቱ የተነሣ የማንም ሕይወት አይጎዳም፡፡ እግዚአብሔርም እንዲሁ ቀድሞ መረጃ (መልዕክት) የሚሰጠን በዚሁ መልኩ ሊጠብቀንና ለሠላማችን ነው፡፡
የመንፈስ ቅዱስ አገልግሎት አካል የሆነው አንዱ ሊመጡ (ሊሆኑ) ያሉትን ቀድሞ ለእኛ መናገር ነው፡፡ እርሱ የእግዚአብሔርን ሃሳብና ለእያንዳንዳችን ሕይወት ያለውን ዕቅድ ያውቃል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- መንፈስ ቅዱስ ወደፊት ሊሆን ያለውን እንድታውቅ እንዲነግርህ ታመነው፡፡