ልብህን ክፈት

«… ኢየሱስም እንባውን አፈሰሰ» (ዮሐ.11፡35) ።

ብዙ ሰዎች ትክክለኛውን መንፈሳዊ ስሜት የማይሰማቸው ናቸው፣ ምክንያቱም በቀደመው ህይወታቸው ብዙ ከባድ ጉዳቶችን አስተናግደው ስለነበር ለዚህም ስሜታቸው በቀላሉ «ዝግ» አድርገውታል። ሰዎች ለረጅም ጊዜ ያህል ምንም እንዳይሰማቸው ዝግ አድረገው ቆይተው እንደገና ወደ ቀደመው ስሜታቸው ለመመለስና ለመጀመር ያሳፍራቸዋል። ምክንያቱም የተጎዱበትን ስሜት መልሰው ስለሚያስታውሳቸው ነው። በመጨረሻ ስሜታዊ ጉዳት መዳኘት (መታየት) ያለበት በመንሳዊ ህይወት በተቃኘ መንፈሳዊ ስሜት እንዲሆን መፍቀድ አለብን። ወደ ቀደመው መንፈሳዊ ስሜት ለመመለስ ስንፈቅድ ከልበ ደንዳናነት ወደ ተሰበረ ልብ (ለቃሉ ወደ ሚንቀጠቀጥ) እንደመለሳለን። ነገር ግን ወደ ቀደመው ስሜታችን ለመመለስ ከእግዚእበሔር ጋር ለመስራት መታገስና ፈቃደኛነትን መግለጥ ይጠይቃል።

የተጎዳውን ስሜትህ መነሻው ምን እንደሆነና እንዴት አስፈሪ እንደነበር ማሰብ ከባድ ቢሆንም በልበ ደንዳናነት እስራት ውስጥ ግን መታሰር ና መቆየት የለብንም። ይህ የችግሮቹን ምልክቶች ብቻ ማከም ይሆናል እንጂ የጉዳትህን ሥር ማግኘት አይሆንም። ይህ ነገም ሊመጣብህ ካለ የበለጠ ጉዳት አይከላከልህም። እንዲያውም የእግዚአብሔርን ድምጽ የመስማት ብቃትህን ይገድበዋል። ልበ ደንዳናነት ከእግዚአብሔር አይደለም፤ እርሱ በጎ ስሜት የሚሰማን አድርጎ ነበር የፈጠረን። በዛሬው በመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል መሠረት ኢየሱስ ራሱ እንዳለቀሰ ይናገራል።

ሁልጊዜ (መቼም) ራስህን በጎ ስሜት የሚሰማው እንዲሆን ፍቀድለት። በስሜት መጎዳት በቀላሉ ልትጎዳ ትችላለህ። ነገር ግን በውስጥህ ያለውን ፈዋሹ ኢየሱስ ሲኖር የተለየ ይሆናል። መቼም ቢሆን ጉዳት ያጋጥምሃል፤ እርሱ ደግሞ የተጎዳኸውን ቁስለት ሊፈውስህ በአጠገብህ በዚያ አለ። ስሜትህን ዝግ ካደረግኸው የእግዚእበሔርን ድምጽ የመስማት ብቃትህ ላይ እያመቻመችህ እንዳለህ ማስረገጥ ነው። እግዚአብሔር እርሱ የሚፈራውን ልብ (የተሰበረ) ልብ እንዲሰጥህና እንዲፈውስህ ለእርሱ ልብህን ክፈት። የእርሱን ድምጽ ለመስማት እንድትችልና ከእርሱ ጋር ባለህ የጠበቀ ህብረት ደስተኛ መሆን እንድትችል ጸልይ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ራስህን ከሰዎች ለመለየትና ከህይወትህ እንዲወጡ ለማድረግ ግምብ የምትሠራ ከሆነ አንተ በራስህ አስራት ታስረህ ከግምቡ በስተጀርባ ታስረህ ትኖራለህ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon