ልትሰጥ የምትችለው ታላቅ ስጦታ

ልትሰጥ የምትችለው ታላቅ ስጦታ

አባታችሁ ርኅሩኅ እንደሆነ እናንተም ርኅሩኆች ሁኑ። – ሉቃ 6፡36

ባሰብኩት ቁጥር የሚገርመኝና የሚያስደንቀኝ አንዳንዴም የሚያስደነግጠኝ በጣም ወሳኝ ነገር ነው፡፡ ቅጣት የሚገባውን ቅጣቱን ትቶ የማይገባቸውን በረከት ሲሰጥ፡፡ ለሌላው ልንሰጥ የምንችለው ታላቅ ስጦታ ነው፡፡

ስጦታውም ምህረት ይባላል። አስቡት ኢየሱስ ወደ ምድር መጥቶ ምህረትን አደረገልን ስለዚህ ለሌሎች ምህረት ማድረግን መማር አለብን፡፡
በክርስቶስ ኢየሱስ ፍቅር የተማርነው ጠላታችንን መውደድ እና ለነርሱ መፀለይ ነው ፤ እኛን የማይወዱትን እንኳ ልንወዳቸውና ምህረት ልናደርግላቸው ይገባል፡፡ ለድሆችና ረዳት አልባ ለሆኑ እርዳታችንን ልንለግሳቸው ከእግዚያብሔር ይህንን ተምረናል፡፡

ስጦታ ሰተናቸው መልሰው ለሚሰጡን ሰዎች ብንሰጥ ምንም አያስገርምም ነገር ግን ለእኛ መልሰው ምንም መስጠት ለማይችሉት ስንሰጥ ግን እንባረካለን፡፡ ይህ ደግሞ ምህረትን ማድረግ ነው፡፡

እግዚያብሔር እንድንሰጥ የሚፈልገው ታላቁ ስጦታ ልክ እንደ ኢየሱስ ምህረትን ማድረግ ነው፡፡ እግዚያብሔር በልጁ በክርስቶስ ኢየሱስ ያደረገልንን አይነት እንከብካቤ ለሌሎች ልናደርግ ይገባናል፡፡ በዙሪያችሁ ላሉ ከእናንተ እናገኛለን ብለው የማይጠብቁትን ታላቁን የይቅርታ ስጦታ ስጧቸው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ በየዕለቱ ስለሰጠኸኝ ምህረትህና ይቅርታህ አመሰግንሃለሁ፡፡ አሁን ለሌሎች ምህረትን ማድረግን ወስኛለሁ ዕድሉን ባገኘሁት አጋጣሚ ሁሉ አንተ እንደተውክልኝ ለሌሎች መተው እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon