መልካሙ እረኛ

መልካሙ እረኛ

መልካም እረኛ እኔ ነኝ፤ በጎቼን ዐውቃለሁ፤ እነርሱም ያውቁኛል። (ዮሐንስ 10፡14)

እግዚአብሔርን ሲናገረን መስማት እንደ አማኞች መብታችን እና ጥቅማችን ነው። እግዚአብሔር ከሌሎች አታላይ ከሆኑ ድምፆች የእርሱን ድምጽ የመለየት ችሎታ ይሰጠናል። በዛሬው ክፍል እንደምናነበው ይህንን ጉዳይ የእረኛቸውን ድምፅ ተፈጥሮአዊ በሆነ መንገድ መለየት ከሚችሉ ከበጎች ባህሪ ጋር ያመሳስለዋል።

በእውነት የእግዚአብሔር ከሆንን ወደ ስህተት ሊመሩን ከሚፈልጉ ድምፆች ድምፁን ለመለየት እንችላለን። የአንድ ነገርን ተፈጥሮ ለመመርመር እና የእግዚአብሔርን ባሕርይ ለማወቅ መማር አለብን።

እግዚአብሔር እንደመልካም እረኛ ሰዎች እያደረጉ ያሉትን እንዲያደርጉ በፍጹም እንደማይነግራቸው የታወቀ ሆኖ ሳለ “እግዚአብሔር ይህን እንዳደርግ ነግሮኛል” ሲሉ ስሰማ በጣም አዝናለሁ። ተጋብተው ሁለቱ በአንድነት እንዲሆኑ እግዚአብሔር እንደወሰነላቸው በመንፈሳዊ መሪዋ የተነገራትን አንዲት ሴት አውቅ ነበር። ችግሩ ቀድሞውኑ ያገባ መሆኑ ነበር። የሚያሳዝነው ነገር ግን እርሷም አምናው አብረው እንዲሆኑ ሚስቱን እንዲፈታ ማበረታታቷ ነበር። ይህ እግዚአብሔርን መፍራት የሌለበት፣ ሞኝነት እና ከቃሉ ጋር የሚቃረን በመሆኑ በጭራሽ የእግዚአብሔር ፈቃድ ሊሆን አይችልም።

ሰዎች ብዙውን ጊዜ “ከእግዚአብሔር እንደሰማሁ እንዴት እርግጠኛ መሆን እችላለሁ?” የሚለውን ማወቅ ይፈልጋሉ። የእርሱን ባህሪ፣ ተፈጥሮ እና እንዴት ከእኛ በፊት ሌሎችን የመራበትን ታሪክ በእውነት የምናውቅ ከሆነ በድምፁ እና በአታላይ ድምፆች መካከል ያለውን ልዩነት ማወቅ እንችላለን። ኢየሱስ ስለ በጎቹ ሲናገር “መቼም ቢሆን [በማንኛውም ሁኔታ] እንግዳ ሰው አይከተሉም፣ የባዕዳንን ድምፅ ስለማያውቁ ወይም ጥሪያቸውን ስለምይለዩ ከእርሱ ይሸሻሉ እንጂ” (ዮሐ 10፡5) ።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ስሜቶች እንዲገዙህ በፍጹም አፍቀድ፤ በተለይ ደግሞ የእግዚአብሔርን ቃል ወይም ባህሪ የሚፃረር ነገር እንድታደርግ የሚመሩህ ከሆነ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon