መልካም ስሮች = መልካም ፍሬ!

እንግዲህ ጌታ ክርስቶስ ኢየሱስን እንደ ተቀበላችሁት እንዲሁ በእርሱ ኑሩ፤በእርሱ ተተክላችሁና ታንጻችሁ፣እንደተማራችሁት በእምነት ጸንታችሁ፣የተትረፈረፈ ምስጋና እያቀረባችሁ ኑሩ፡፡ – ቆላ 2፡6-7

ባህሪያችን የሚመጣው ከሆነ ነገር መሆኑን ማወቅ አስፈላጊ ነው፡፡መጥፎ ባህሪ ከመጥፎ ስር ካለው መጥፎ ዛፍ እንደሚፈራ መጥፎ ፍሬ ነው፡፡

ዕድሜ ዘመናችሁን ሁሉ ከውጫዊ ስሜቶቻችሁ ጋር በመታገል ልታሳልፉ ትችላላችሁ ነገር ግን ስሩ ካልተነቀለ መጥፎው ፍሬ ሌላ ቦታ ይወጣል፡፡መርሁ አይቀየርም፡የተበላሹ ፍሬዎች የሚበቅሉት ከተበላሹ ስሮች ነው፣ጥሩ ፍሬዎች ደግሞ የሚገኙት ከመልካም ሰሮች ነው፡፡

መጥፎ ፍሬዎችን መፍትሄ ለመስጠት ጳውሎስ ለቆሮንቶስ ሰዎች የሰጠውን በእግዚአብሔር “ሥር ስደዱ” የሚል ተግሳጽ መከተላችሁ ግድ ነው::

የራሳችሁን ስር በጥንቃቄ ልትመረምሩ ይገባል፡፡የማያስደስቱ፣ጎጂ ወይም አጥቂ ከሆኑ ተስፋን አትቁረጡ፤ከዛ መጥፎ አፈር ላይ ተነቅላችሁ በእርሱ እና በፍቅሩ ስር እንድትሰዱ የክርስቶስ ኢየሱስ መልካም መሬት ላይ መተከል ትችላላችሁ፡፡

አስታውሱ መነቀል ህመም ሊኖረው ይችላል፡፡እንደገና ተተክሎ ስር መስደድ ጊዜ እና ጥረት የሚጠይቅ ሂደት ነው፡፡ነገር ግን የእግዚአብሔርን የተስፋ ቃላት የምንውርሰው በእምነት እና በትዕግስት ነው፡፡

የምጸልይላችሁ በክርስቶስ ጠልቃችሁ በመተከል ስር ሰዳችሁ በሄዳችሁበት ሁሉ መልካምን ፍሬ እንድታፈሩ ነው!


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ ስሬን መልካም ስሮች ያሉት መልካም ፍሬን የሚያፈራ መልካም ዛፍ እሆን ዘንድ ከመጥፎ አፈር ላይ ተነቅዬ በክርስቶስ ጠልቄ እንድተከል እርዳኝ፡፡የሚያም ሊሆን እንደሚችል አውቃለሁ ነገር ግን በእምነት እና በትዕግስት ህይወቴ ላይ ለውጥ እንዳመጣ ልትረዳኝ እንደምትችል አምናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon