መልካም የሆነው እግዚያብሔር ለምን ነው ክፉ ነገሮች እንዲሆኑ የሚፈቅደው?

መልካም የሆነው እግዚያብሔር ለምን ነው ክፉ ነገሮች እንዲሆኑ የሚፈቅደው?

በጎ ስጦታና ፍጹም በረከት ሁሉ ከላይ ከሰማይ ብርሃናት አባት ይወርዳሉ፤ በእርሱ ዘንድ መለዋወጥ ከመዞር የተነሣ የሚያርፍ ጥላም የለም። – ያዕቆብ 1፡17

በችግርና በመከራ ውስጥ በምንሆንበት ጊዜ በእግዚያብሔር ላይ ማጉረምረም የተለመደ ነገር ነው፡፡ እግዚያብሄር ሁሉን ቻይ ከሆነ፣የፍቅር አምላክ ከሆነና መልካም ከሆነ ለምን ነው በህመም ውስጥ እንድናልፍ የሚፈቅደው ለምን አያስቆመውም? በማለት በተደጋጋሚ ሰዎች ይጠይቃሉ፡፡

ሰይጣን መገንባት የሚፈልገውን ግንብ የሚገነባበት ብቸኛው ቀዳዳ ይኼኔ ነው፡፡ ሰይጣንም እግዚያብሔር መልካም አይደለም ሊታመንም አይገባውም የሚለውን ፕሮፖጋንዳውን ይነዛል፡፡ እውነቱ ግን ያለው ሰይጣን ጋር ሳይሆን የእግዚያብሔር ቃል ውስጥ ነው፤ እኛ እግዚያብሔር እውነተኛ እንደሆነ እናምናለን፡፡ ሰይጣን የውሸት አባት ነው እሱ ውሸታም ነው፡፡

ያዕቆብ 1፡17 በደንብ አንብቡት ሁሉም መልካም ነገር የሚመነጨው ከእግዚያብሔር ነው፡፡ እግዚብሔር መልካም ነው ሌላ ነገር ፈፅሞ ሊሆን አይችልም፡፡ እሱ አይለወጥም፡፡ እሱ ፍፁም የማይናወጥና መልካም የሆነ ሁል ጌዜም መልካም የሆነ አምላክ ነው፡፡

እግዚያብሔር ሁል ጊዜ መጥፎ ነገሮች እንዲቆሙ አለማድረጉ ግልፅ ነው ፣ በእውነቱ መጥፎ ነገሮች ለምን እንደሚፈጠሩ አናውቅም፡፡ 1ቆሮ 13፡12 እንደሚለው አሁን የምናየው በመስተዋት ውስጥ እንደሚታይ በድንግዝግዝ ነው። ሁል ጊዜ ማወቅ ያለብን እምነት ያልተመለሱ ጥያቄዎችንም እንድንቀበል ይፈልጋል፤ ሁሉን የሚያውቀውን በማወቃችንና እምነታችንን በርሱ ዘንድ በማድረግ ወደምንደሰትበት ቦታ መምጣት እንችላለን።


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ለምን ክፉ ነገሮች እንደሚሆኑ ሁል ግዜ ልረዳ አልችልም ነገርግን አንተ መልካም መሆንህን አውቃለሁ ለምን እንደሆነ ባላውቅም በአንተ ግን እፅናናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon