መመራት ያስፈልጋል

መመራት ያስፈልጋል

ምክንያቱም ጌታ የሚወደውን ይገስጻል፤እንደ ልጅ የሚቀበለውንም ይቀጣል፡፡ – ዕብራ 12፡6

ከጌታ ጋር ካለኝ ህብረት ውስጥመውጣት አልፈልግም፡፡በእያንዳንዱ በህይወቶቼ ቀኖች ውስጥ ለማለፍ እርሱ ያስፈልገኛል፡፡

ለዚህ ነው ለሚመራኝ መንፈስ ቅዱስ ምስጋና ያለኝ፡፡እግዚአብሔርን የሚያሳዝን ወይም ግንኙነታችንን ሚያውክ ነገር ሳደርግ ያሳውቀኛል፡፡መርቶ ትክክለኛው ነገር ምን እንደሆነ ያሳምነኛል፡፡

እግዚአብሔር እኛ ልጆቻችንን ከምንወደው እንኳ በላይ ይወደናል እና በፍቅሩ ደግሞ ስርዐትን ያስይዘናል፡፡በተሳሳተ መንገድ ላይ ስንጓዝ ይነግረናል፡፡አስፈላጊ ከሆነ ትኩረታችንን ለማግኘት በአስራ አምስት የተለያዩ መንገዶች ሊነግረን ይችላል፡፡

በፍቅር የሚመራን መልዕክቱ በየቦታው አለ፡፡ስለሚወደን እንድንሰማው ይፈልጋል፡፡ነገር ግን በመንገዳችን ከጸናን እንድናድግ እና ለእኛ መልካም የሆነውን እንድናገኝ ስለሚፈልግ በረከቶቻችንን እና ጥቅሞቻችንን መያዝ ይጀምራል ፡፡

ለመመራት ራሳችሁን ከሰጣችሁ ከሀጢያት አውጥቶ ከፍ ያደርጋችሁና ወደ እግዚአብሔር ልብ ይመልሳችኋል፡፡

በመመራት፤ በእግዚአብሔር ወደ ሌላ ደረጃ ይውሰዳችሁ፡፡አትቋቋሙት፤ተቀበሉት፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ እንደምትወደኝና ለእኔ ምርጡን እንደምትፈልግ አውቃለሁ፡፡ሀጢያትን ስሰራ ወይም ስሳሳት ስለምታርመኝ እና ስርዐት ስለምታስይዘኝ አመሰግናለሁ፡፡በምችለው መጠን ሁሉ ወደ አንተ መቅረብ እፈልጋለሁ፡፡በእኔና በአንተ መሀከል ምንም እንዳይገባ እርዳኝ፡፡እወድኃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon