መስዋዕትን ሠዋ

‹‹ … እንግዲህ ዘወትር ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት፥ ማለት ለስሙ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ፥ በእርሱ እናቅርብለት›› (ዕብ.13፡15) ።

በዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍል እንደተጠቀሰው ‹‹የምሥጋና መስዋዕት›› የሚለው ብዙውን ጊዜ የሚተረጎመው እርሱን እንዳመሰገነው በማይሰማን ጊዜ እግዚአብሔርን ከማመስገን በላይ የሚበልጥ ነገር እንደሌለ ብለን እንተረጉመዋለን፡፡ የዕብራውያን ጸሐፊ የብሉይ ኪዳንን የመስዋዕት ሥርዓት በመጥቀስ የእንስሳት ደም የሰዎችን ኃጢአት ለማስተሰረይ መስፈርት እንደሆነ አምናለሁ፡፡

ይሁንም እንጂ እኛ በአዲስ ኪዳን ውስጥ የምንኖር በመሰዊው ላይ አስቀምጠን በግ፣ ፍየልና ወይፈን ማረድ ከዚህ በኋላ አያስፈልገንም፡፡ በዚህ ፈንታ በዚህ ዘመን እግዚአብሔር ከእኛ የሚፈልገው መስዋዕት ለእግዚአብሔር የሚቀርበው ከአፋችን የሚወጣ መልካም ቃል መስማትን ነው፡፡ በብሉይ ኪዳን ዘመን ፊት የእንስሳት መስዋዕት መዓዛና ጢስ በእርሱ ዙፋን እንደሚወጣ፤ ዛሬም ከልባችን የሚወጣው ምስጋና ወደ እርሱ ፊት ይወጣል፡፡ በዕብ.13፡15 መሠረት ጌታ በትክክል እንዲህ ይላል ‹‹… እኔ አሁን የምፈልገው መስዋዕት ለስሜ የሚመሰክሩ የከንፈሮችን ፍሬ ለእግዚአብሔር የምስጋናን መሥዋዕት ነው››፡፡

እኛም ይህንን የመጽሐፍ ቅዱስ ቃል በእያንዳንዱ ቀን ህይወታችን ልንተገብረው ያስፈልገናል፤ የእግዚአብሔርን ምስጋና ባገኘን አጋጣሚ ሁሉ መናገራችንን እርግጠኛ መሆን ይገባናል፡፡እርሱ ለእኛ እያደረገ ያለውን ታላቅ ነገሮች ለሰዎች መናገር ያስፈልገናል፤ እርሱን ማመስገንና እንደምንወደውም ለእርሱ መናገር ያስፈልገናል፡፡በልባችንና በአንደበቶቻችን በቀጣይነት እንዲህ ልንል ይጠበቅብናል ‹‹ጌታ ሆይ እወድሃለሁ፣ በህይወቴ እያደረግህ ስላለው ሁሉ ነገር እጅግ አመሰግንሃለሁ፤ ጌታ ሆይ ዛሬ ለእኔ በተመለከተ እያደረግህ ስላው እንክብካቤ ሁሉ አመሰግንሃለሁ›› እኛ የምስጋና ሰዎችና ‹‹በቋሚነትና ሁልጊዜ›› ለእግዚአብሔር እውቅና የምንሰጥ መሆን ያስፈልገናል፤ የምስጋና መስዋዕት ወደ እርሱ በቀጣይነት ማረግ ያስፍልገናል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ የዛሬም እእንደሁልጊዜው ለእግዚአብሔር ምስጋና ማቅረብ እንችላለን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon