‹‹ … ለዋኖቻችሁ ታዘዙና ተገዙ፤ እነርሱ ስሌትን እንደሚሰጡ አድርገው፥ ይህንኑ በደስታ እንጂ በኃዘን እንዳያደርጉት፥ ይህ የማይጠቅማችሁ ነበርና፥ ስለ ነፍሳችሁ ይተጋሉ›› (ዕብ.13፡17) ።
በዚህ ዘመናዊው ዓለም ህብረተሰቡ ፍጹም በሆነ ዓመጽ ተሞልቷል፡፡ ዓመጽ ደግሞ እግዚአብሔርነ እንዳንሰማ ያደርጋል፡፡ እኔ በብዙ የተመለከትኩትና የታዘብኩት ብዙ ብዙ ሰዎች ከስለጣን ጋር በተያያዘ ብዙ ግጭት ውስጥ ሆነው ይገኛሉ፡፡ ይህም በጋብቻ ውስጥ፣ በቤተሰብ፣ በንግዱ ዓለም፣ በሲቪል እንቅስቃሴ፣ና በሁሉም ባህሎች ውስጥ የሚታዩ እውነት ነው፡፡ ለመንፈሳዊ ባለስልጣን አለመታዘዝ በተለየ ሁኔታ እየታየ አይደለም፡፡
ብዙ ጊዜ አንድ መጋቢ የሰዎችን አንዳንድ ስህተት ለማረም ከሞከረ ሰዎች ወደ ብጥብጥና ኩርፊያ ያዘነብሉና ቤተክርስቲያንን ለቅቀው ለመሄድ ይሞክራሉ፡፡ ይህ ደግሞ ትክክል አይደለም፡፡ ጳውሎስ በተደጋጋሚ ብዙውን ጊዜ ሰዎች ያርም ነበር፤ ይህ ደግሞ እንደ አንድ መንፈሳዊ መሪ አንዱ ሥራው ስለሆነና ህ ዛሬም ድረስ የቀጠለ መንፈሳዊ መሪዎች ኃላፊነት ነው፡፡ ጳውሎስ እንዲህ ይላል ‹‹ … ለደስታችሁ ከእናንተ ጋር የምንሠራ ነን እንጂ፥ በእምነታችሁ በእናንተ ላይ የምንገዛ አይደለንም። በእምነታችሁ ቆማችኋልና››(2ኛቆሮ.1፡24) ። ለመንፈሳዊ ባለስልጣን መኖር ለደስታችን መብዛት መሆኑን ስንረዳና ስናውቅ እንቀበለዋለን፤ እናደርገዋለን፡፡ ደስታችንም ይጨመራል፡፡ ስለዚህ እግዚአብሔርን የመስማት ብቃታችንም ይጨምራል፡፡
እንደ 2ኛተሰ.2፡7 – 8 መሠረት ዛሬ በዓለም ላይ እየሠራ ያለው የዓመጽ መንፈስ የክርስቶስ ተቃዋሚ (የሐሰተኛ ክርስቶስ) መንፈስ ነው፡፡ ይህ ለማንም ሰው ለመታዘዝ ፈቃደኛ ያልሆኑ ማለት ነው፡፡ ዛሬ ሰዎች መብታችንን መጠየቅ ብለው ይከራከራሉ፡፡ ነገር ግን እውነታው አብዛኛውን ጊዜ ባለስልጣናትን በመቃወም የራሳቸውን ከፍ ያደርጋሉ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ለጌታ እንደምታገለግል ለባለስልጣን ታዘዝ (ተገዛ) እርሱ ደግሞ ይባርክሃል፤ ያበለጽግሃል፡፡