
ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ በእናንተ ላይ በሚወርድበት ጊዜ ሀይልን (ችሎታን፣ብቃትን እና ጉልበትን) ትቀበላላችሁ… – ሐዋ 1፡8
በሐዋሪያት 1፡8 ላይ ኢየሱስ መንፈስ ቅዱስ በእኛ ላይ እንደሚመጣ እና እስከ ምድር ጫፍ ድረስ የክርስቶስ ምስክሮች እንድንሆን ሀይልን (ችሎታን፣ብቃትን እና ጉልበትን) እንደሚሰጠን የተስፋ ቃሉን ሰጥቶናል፡፡
ብዙ ክርስትያኖች ሁሉንም “ትክክለኛ ደንቦች” ይከተሉና ይሄ ብቻ ነው? ሲሉ ይጠይቃሉ፡፡ እንደ ወጣት ክርስቲያን ያ ተመሳሳይ ባዶነት አጋጥሞኝ ነበር፡፡ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ጊዜያዊ ደስታን ያመጣል ነገር ግን ጥልቅ የሆነ አርኪ ደስታ የለውም፡፡
“እግዚአብሔር ሆይ የሆነ ነገር ጎሏል!” ብዬ ጮሀኩ ለራሴ እስኪገርመኝ ድረስ ከጥቂት ሰአታት በኋላ ኢየሱስ ከዚህ በፊት ሞክሬው በማላውቀው መንገድ በመንፈስ ቅዱስ ህልውና ሞላኝ እናም ሁሉም ነገር ተለወጠ፡፡ሀይሉ በህይወቴ ውስጥ በተለየ መንገድ ይታወቀኝ ጀመር፡፡
ከእግዚአብሔር ጋር በየቀኑ ጊዜ ስታሳልፉ እና ቅዱሱንመንፈሱን ስትቀበሉ አስፈሪ እና ደባሪ ተሞክሮ አይኖራችሁም፡፡የበለጠ ኢየሱስን ለመምሰል እና የተለመዱ ነገሮች ውስጥ ለማለፍ የሚረዳውን የእርሱን ሀይልና ጥበብ እየተቀበላችሁ ነው፡፡
አዳዲስ ነገሮችን አትፍሩ-መጽሀፍ ቅዱሳዊ መሆናቸውን ብቻ እርግጠኛ ሁኑ፡፡እግዚአብሔር በራሱ ወደ አዳዲስ ከፍታዎች ከመንፈስ ቅዱስ ጋር በሚኖራችሁ የዕለት ተዕለት ግንኙነት ውስጥ ባለው ሀይል ሊወስዳችሁ እንደሚፈልግ አምናለሁ፡፡የልባችሁን በር እያንኳኳ ነው፡፡በሰፊው ከፍታችሁ ትቀበሉታላችሁ?
የጸሎት መጀመሪያ
እግዚአብሔር ሆይ በመንፈስ ቅዱስህ ሀይል የተሞላ ክርስቲያን ሆኜ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ከመንፈስ ቅዱስ በሚመጣ ጥልቅ እና አርኪ ደስታ ውስጥ እንዴት መኖር እንደምችል አሳየኝ፡፡በእያንዳንዱ ቀን እና በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ በጽድቅህ፣በሰላምህ እና በደስታህ ስለማልፍበት ሀይልህ እና ጥበብህ አመሰግናለሁ፡፡