መንፈስ ቅዱስ ለአንተ ይማልዳል

እንዲሁም ደግሞ መንፈስ ድካማችንን ያግዛል፣ እንዴት እንድንፀልይ እንደሚገባን አናውቅምና ነገር ግን መንፈስ ራሱ በማይነገር መቃተት ይማልድልናል፡፡ ሮሜ 8 26

የእግዚአብሔር ቃል እንደሚያስተምረን የእግዚአብሔር መንፈስ ብቻ በትክክል የእግዚብሔርን ሃሣብ ስለማያውቅ እርሱ በምልጃና በፀሎታችን ሊማልድልንና ሊመራን ያስፈልጋል፡፡

እንደ እግዚአብሔር ፈቃድ ለመፀለይ እንደ እኔ እምነት ከሆነ አንተ ማድረግ ያለብህ የእግዚአብሔርን ሃሣብና ፈቃድ ማወቅ አለብን፡፡ ብዙውን ጊዜ የምንረዳቸው ነገሮች አሉ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ያውቃል፡፡ ስለዚህ እርሱ በእኛ ፋንታ ይማልዳል፡፡ እኔ በበኩሌ የእራሴን ድርሻ በፀሎቴ አደርጋለሁ፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስን ማመስገን ያለብኝ በፀሎቴ አብሮኝ ያለና ለእኔም ስለሚፀልይልኝ ነው፡፡ በእግዚአብሔር ቃል በኩል እንደምናውቀው ምንም ነገር በሕይወታችን ቢገጥመንም እኛ በፀሎትና በእርሱ ፍቅር ውስጥ እስከ ቆየንና እርሱን ፈቃድ እስከፈለግን ድረስ እግዚአብሔር ነገርን ሁሉ በመልካም እንደሚያደርግልን እንታመናለን፡፡

የዛሬው ጥቅስ ሮሜ 8 26 በፍጥነት በሮሜ 8 28 እንዲህ በሚል ነው ‹‹እግዚአብሔርን ለሚወዱት እንደ ሃሣቡም ለተጠሩት ነገር ሁሉ ለበጎ እንዲደረግ እናውቃለን፡፡ ‹‹እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን የላከልን በማንኛውም ነገርና በፀሎም እንዲረዳን እንደላከልን ማወቅ ምን ያህል ምቾት ይሰጠን ይሆን፡፡ የትኛውም ነገራችንን ለመልካም የማያደርግበት ሁኔታ የለም፡፡ ዛሬ በፀሎትህ መንፈስ ቅዱስ እንዲረዳህ ጠይቀው፡፡ ምንም እንኳ ጉዳትህ ጥልቅና የማያቃስትህ ሆኖ የምታደርገውንም ነገር ብታጣ መንፈስ ቅዱስ ግልፅ አድርጎ በትክክል ለእግዚአብሔር በማቅረብ መልስ እንድታገኝ ያደርጋል፡፡ መለኮታዊ አጋዥ አለህ ሁልጊዜ ከአንተ ጋር የሆነ ስለዚህ ሁልጊዜ እርሱን አዘውትረህ ጥራው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- መንፈስ ቅዱስ በትክክል እንደማያማልድህ ልትታመነው ትችላለህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon