ነገር ግን የእውነት መንፈስ እንጂ ከራሱ አይናገርምና የሚመጣውንም ይነግራችኋል፡፡ ዮሐ 16÷13
እግዚብሔር መንፈስ ቅዱስን ወደሰው ሕይወት እነዲሰራ ሲልክ እርሱ በኃጥያት ላይ ይፈርዳል እንጂ በኃጥያተኞች ላይ አይፈርድም፡፡ በሁሉም የእግዚአብሔር ቃል ውስጥ ግልፅ የሆነ ለግለሰቦች ሁሉ ያለውን ፍቅሩን እናያለን፡፡ የእርሱ ፍላጎት ለሕዝቡ ኃጥያታቸውን ወደኋላ ትተው ወደፊት እርሱ ለእነርሱ ሕይወት ያለውን ትልቅ ዓላማ ውስጥ እንዲገቡ ነው፡፡ እርሱ ምን ዓይነት ስህተት እንደሰራን እንዲነግረንና እንዲያሳየን መፍቀድ እንጂ ፈፅሞ መፍራት አይገባንም፡፡
መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ ሲኖር የእርሱ ሥራ እኛን መምራት፣ ማስተማር፣ መርዳት፣ በፀሎት ማገዝ እኛን ማደላደል፣ ስለኃጥያት እኛን መውቀስ፣ የእግዚአብሔር ፈቃድ በሕይወታችን እንዲፈፀም እኛን መምራት ነው፡፡
መንፈስ ቅዱስን መታመን አለብን፡፡ ምክንያቱም እርሱ በትክክል ምን በሕይወታችን መሆን እንዳለበት ትክክለና ጊዜውን ያውቃልና ነው አንተም ‹‹እኛ ስብርባሪ ነን›› እርሱ ግን እንዴት እንደሚጠግነን ያውቃል ማለት አለብህ፡፡
መንፈስ ቅዱስ ከሁላችን ጋር እንዲሆን ሁሉ በሕይወትህ ጉዳዮች ውስጥ ሆኖ ከአንተ ጋር በብዙ ጉዳዮች እንደሚሠራ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ምክንያቱም እርሱ የሚደርገውን ያውቃል በትክክልም ደግሞ ያደርጋል፡፡ ሰዎች እኛን መጠገን ወይም እኛ እራሳችንን መጠገን ብንሞክር ነገሮችን የባሰ እናበላሻለን፡፡ ነገር ግን መንፈስ ቅዱስ ሚስጥራዊና በሚያስደንቅ መንገድ ያከናውናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ መንፈስ ቅዱስ የምሠራውን ሳናውቅ ወይም ላንወደው እንችላለን፡፡ ነገር ግን መጨረሻው አስደሳች ነው፡፡ እራስህን ለቀቅ ዘና አድርገህ በሠራልህና ለሚሠራልህ ሁሉ በምስጋና በፊቱ ተመላለስ
የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ለመንፈስ ቅዱስ እንዲቀጥል ቀጥልበት