መፀለይ አለብን

ነገር ግን በምንም ሳይጠራጠር በእምነት ይለምን፣ የሚጠራጠር ሰው በነፋስ የተገፋና የተነቃነቀ የባሕርን ማዕበል ይመስላል፡፡ ያዕ 1 6

የአዲስ ኪዳን የሆነው የያዕቆብ መልዕክትን ብናነብ ያዕቆብ የሚጀምረው የሕይወት ተሞክሮና ችግሮችን እንዴት መያዝ እንዳለብን በመናገር ነው፡፡ እነዚህን ነገሮች በተፈጥሮአዊ መንገድ መያዝ ወይም ማስተናገድ የሚቻል ሲሆን ነገሮች በተፈጥሮአዊ መንገድ መያዝ ወይም ማስተናገድ የሚቻል ሲሆን ነገር ግን ደግሞ መንፈሳዊ የሆኑ ነገሮችን የመያዝና የመቆጣጠር መንገድም አለ፡፡ በያዕቆብ 1 5-6 በመሠረቱ ያዕቆብ የምለው ‹‹በችግር ውስጥ ከሆንክ ምን ማድረግ እንዳለብህ እግዚአብሔርን ጠይቅ›› ነው፡፡ ምናልባት የእርሱን ድምፅ ስትሰማና ቶሎ ብለህ መልስ ሳታገኝ ትችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን በእምነት ብትጠይቅ መንገድህን እየሄድክ የዕለት ጉዳዮችህን እያከናወንክ እያለህ በመለኮታዊ ቅባቱ በኩል ከአንተ ተፈጥሮአዊ እውቀት በላይ በሆነ መንገድ በሕይወትህ ስንቀሳቀስ ታገኛለህ፡፡

በመዝሙር 23 2 ላይ ዘማሪው እግዚአብሔር ሕዝቡን በለመለመ መስክና በእረፍት ውሃ ዘንድ እንደሚመራቸው ይናገራል፡፡ በሌላ አነጋገር እግዚአብሔር እኛ ስንፈልገው ሁልጊዜ በሠላም ሥፍራ እና በእርካታ ሕይወት ይመራናል፡፡

ወደ ዛሬው ጥቅስ ስንመለስ በእምነት መጠየቅ እንዳለብን እናስተውላለን፡፡ ለምንሰራቸው ነገሮች ሁሉ እርዳታ አናገኝም፡፡ ምክንያቱም ለዛ ነገር እገዛና እርዳታ ለመጠየቅ ስለማንችል ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስ ጨዋ ስለሆነ እኛ እሱን እስክንጋብዘው ድረስ በሁኔታችን ውስጥ ጣልቃ በመግባት ይጠብቀናል፡፡ እኛ መጠየቅ ወይም መለመን እንዳለብን ጨርሰን አናስበውም ደግሞም አንገምተውም፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- አንድን ነገር ስትፈልግ በመጀመሪያ ስለዛ ጉዳይ እግዚአብሔርን ጠይቅ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon