
እንግዲህ ወንድሞች ሆይ በመረቀልን በአዲስና በሕያው መንገድ ወደ ቅድስት በኢየሱስ ደም በመጋረጃው ማለት በሥጋው በኩል እንድንገባ ድፍረት ስላለን፡፡ ዕብ 10 19-20
ኢየሱስ በሞተ ጊዜ የቤቴ መቅደስ መጋረጃ መቅደሱንና ቅድስት ቅዱሳኑን ይለይ የነበረው ከላይ ወደታች ተቀደደ (ማር 15 34-39 ተመልከት) ማንኛውም ሰው ወደ እግዚአብሔር መገኛ ለመግባት እንድችል ተከፈተለት፡፡ ከክርስቶስ ሞት በፊት ግን ሊቀ ካህኑ ብቻ እግዚአብሔር ወደሚገኝበት በዓመት የእንስሳትን ደም ይዞ ይገባ ነበር፡፡ ይህም ለራሱ ኃጥያትና ለሕዝቡ የኃጥያት ስርአትን ለመቀበል ነው፡፡
የመጋረጃው ከላይ ወደታች መቀደድ የራሱ የሆነ ትርጉም አለው፡፡ መሸፈኛው ወይም መጋረጃው በጣም ከፍ ያለና በጣም ወፍራም ከመሆኑ የተነሣ መቀደድ አይችልም፡፡ የተቀደደው በመለኮታዊ የእግዚብሔር ኃይ ሲሆን ይህ ደግሞ የሚያሳየው እግዚአብሔር ለሕዝቡ አዲስና ሕያው መንገድ ወደ እርሱ የሚቀርብበት መንገድ መክፈቱን ነው ከዛሬ የንባባችን ጥቅስ የምናነበው፡፡
ከቀድሞ እግዚብሔር ከሰው ልጆች ጋር ሕብረት ማድረግ ይፈልጋል፡፡ እኛን ሲፈጥረንም ዓላማው ይህ ነበር፡፡ ሰዎችን ከመገኘቱ ለማራቅ ፈልጎ አያውቅም፡፡ ነገር ግን እርሱ የቅድስናው ታላቅነት ነገሮችን ሁሉ ከቅድስናው ጉድለት የተነሣ ሊያጠፋ እንደሚችል ስለሚያውቅ እንዳይቀርቡ ይከላከላል፡፡ ለዚህም ኃጥያተኞች ሙሉ በሙሉ ከኃጥያታቸው የሚነፁበት መንገድና ወደ እግዚአብሔር መገኘት የሚቀርቡበት ቅድመ ሁኔታ አቀረበላቸው፡፡
እኛ በዓለም ብንሆንም ነገር ግን የዓለም አይደለንም፡፡ (ዮሐ 17 14-16) የእኛ አለማዊነትና ሥጋዊነት ከእግዚአብሔር ጋር ለመገናኘት እንዳንችል ያደርገናል፡፡ እንዲሁም ደግሞ የእርሱን ድምፅ ከመስማት ይከለክለናል፡፡ የኢየሱስን ደም መስዋዕት ካልተቀበልንና በቀጣይነት እንደሚያነፃን በእምነት ካልተቀበልን ከእግዚአብሔር ጋር በጠበቀ ኅብረት ለመኖር ያስቸግረናል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር ከአንተ ጋር ኅብርት ማድረግ ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ ወደ መገኘቱ ዛሬ ሆነህ ግባ፡፡