ምን እናድርግ?

ምን እናድርግ?

በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ተስፋ ካልቆረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን፡፡ – ገላ 6፡9

በምንኖርበት አለም ሁሉንም አይነት ችግሮች፣ተስፋ መቁረጦች እና አስቸጋሪ ነገሮች እንጋፈጣለን፡፡ይሄ ህይወት ነው፡፡ታዲያ ምን እናድርግ?

ጸንተን ልንቆም ይገባል፡፡በሌላ ቃላት መልሱ በፍጹም ተስፋ አለመቁረጥ ነው! በህይወታችን እያለፍንብት ያለው ነገር ምንም ይሁን ምን ድላችን ያለው በመጽናታችን ውስጥ ነው፡፡

በከፍተኛው የትግላችን ወቅት መንፈስ ቅዱስ ምናልባትም ትልቅ ስራ በውስጣችን እየሰራ ሊሆን እንደሚችል አስቡ፡፡ ሁኔታዎች እርሱን አያውኩትም፡፡እኔ እና እናንተ የእውነት ከታመንንበት፣እኛም መታወክ አይገባንም! በህይወታችን ውስጥ ያለው ለመልካም ጊዜያት ብቻ አይደለም ለአስቸጋሪዎቹም ጊዜያት ጭምር እንጂ፡፡

ዝም ብለን ከተከተልነው በማናቸውም ነገር ውስጥ ይመራናል፡፡ይሄም ማለት በጸሎት በመትጋት፣መፍትሄ ፍለጋችንን በጽናት በመቀጠል፣በእምነታችን ባለመናወጥ እና በእግዚአብሔር ቃል እና በተስፋ ቃሎቹ ላይ ጸንተን በመቆም ነው፡፡

በጣም ብዙ ጊዜ ነገሮች እንዴት በዝግታ እንደሚሄዱ በማየት እንሰናከላለን፡፡በእርግጥም ጠላት ለእኛ ይሄንን ማመልከት በጣም ይወዳል! ነገር ግን አስታውሱ፣ ምናልባትም እግዚአብሔር ይህንን ተጠቅሞ አንዳንድ ታላላቅ ስራ እየሰራ ይሆናል፡፡አያችሁ ጉዳዩ ስለ እኔ እና ስለ እናንተ ብቻ አይደለም፡፡እግዚአብሔር በእኛ የሚሰራው ስራ በእኛ ሊሰራ ለሚፈልገው ነገር ማዘጋጀትም ነው!

አንዳንዴ ህይወት ከባድ እንደሚሆን አውቃለሁ፡፡ ግን ደግሞ ጸንተን ከቆምን እግዚአብሔር እንደሚረዳንም አውቃለሁ፡፡በገለቲያ 6፡9 ላይ እንቁም፤በጎ ነገር ከማድረግ አንታክት፤ተስፋ ካልቆረጥን ጊዜው ሲደርስ መከሩን እናጭዳለን፡፡

ስለዚህ ደግሜ ያንን ጥያቄ ልጠይቃችሁ፡ምን እናድርግ? መልሴ በፍጹም ተስፋ አትቁረጡ!ነው፡፡የእናንተስ መልስ ምን ይሆን?


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ፣በአስቸጋሪ ጊዜም እንኳ በእኔ ህይወት በስራ ላይ ነህ ብዬ አምናለሁ፡፡ዛሬ ጸንቶ ለመቀጠል እና አንተን በመታዘዝ ላይ ተስፋ ላለመቁረጥ እመርጣለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon