ራስህን መቀበል ጨምር

ራስህን መቀበል ጨምር

የእምነትህም ኅብረት፥ በእኛ ዘንድ ያለውን በጎ ነገር ሁሉ በማወቅ፥ ለክርስቶስ ኢየሱስ ፍሬ እንዲያፈራ እለምናለሁ፡፡ – ፊሊሞና 1:6

ንተ ስለራስህ ከፍ አድርገህ አታስብ ይሆናል ነገር ግን እግዚአብሔር አንተ በክርስቶስ እንደሆንክና ራስህንም እንደምትመስል እንድታዉቅ ይፈልጋል፡፡ ከዚህ በታች አንተ በክርስቶስ ማን እንደሆንክ እንድትረዳና ራስህን መቀበልንና በራስ መተማመንህን እንድታገኝ የሚረዱህ አምስት ጉርሻዎች ተዘርዝረዋል፡፡

  1. ስለራስህ አሉታዊ ነገር ፈጽሞ አትናገር፡ የእምነትህ ተግባቦት ዉጤታማ የሚሆነዉ በክርስቶስ ኢየሱስ በኩል በአንተ ዉስጥ ያለዉን መልካም ነገር ሁሉ ዕዉቅና በመስጠት እንጂ በራስህ ድካምና ጉድለት ላይ በማተኮር አይደለም፡፡
  2. ራስህን ከሌሎች ጋር ማነጻጸርን አስወግድ፡ ጴጥሮስ ራሱን ከሌሎች ደቀ መዛሙርት ጋር ሲያነጻጽር ይህ ዕንቅፋት ገጥሞታል፡፡ እንዲህ ብሏል …“ጌታ ሆይ እርሱስ?” ኢየሱስም ሲመልስለት “እስክመለስ ድረስ በሕይወት እንዲኖር ብፈልግ አንኳ አንተን ምን ቸገረህ” ነዉ ያለዉ (ዮሐ 21፡21-22)፡፡ እኛ የተጠራነዉ ለማነጻጻር ሳይሆን ለመታዘዝ ነዉ፡፡
  3. የአንተን ዋጋ እግዚአብሔር ይወስነዉ፡ አስታዉስ ከኢየሱስ የተነሳ አንተ ቀድሞዉኑ በእርሱ ተቀባይነት አግኝተሃል፡፡
  4. ጉድለቶችህን አስብ፡ የቱ ጋር ማሻሻል እንዳለብህ ማየት ጥሩ ነዉ ነገር ግን ለዉጥህን ማድነቅ እንዳትዘነጋ፡፡
  5. እዉነተኛ በራስ የመተማመን ምንጭ ፈልግ፡ በራስ መተማመንህ ከእግዚአብሔር ከሆነ ጤናማ አመለካከት አለህ፡፡ የተሻለዉን አድርግ እናም ቀሪዉን ለእርሱ ተወዉ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! እኔ ራሴን መቀበል ሲከብደኝ እንኳ ስለተቀበልከኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ አንተ የሰጠሀኝን በጎ ነገር ማድነቅ እንድችል እባክህ እርዳኝ፤ ደግሞም በራስ መተማመኔ በአንተ ነዉና መንገዴን እንዳሰብክልኝ እንድጓዝ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon