ራስህን በመባ ሳህኑ ላይ አኑር

ራስህን በመባ ሳህኑ ላይ አኑር

እንግዲህ፥ ወንድሞች ሆይ፥ ሰውነታችሁን እግዚአብሔርን ደስ የሚያሰኝና ሕያው ቅዱስም መሥዋዕት አድርጋችሁ ታቀርቡ ዘንድ በእግዚአብሔር ርኅራኄ እለምናችኋለሁ፥ እርሱም ለአእምሮ የሚመች አገልግሎታችሁ ነው። – ሮሜ 12፡1

በ 2 ቆሮ 8 ላይ ጳውሎስ ለቆሮንቶስ አማኞች ስለ ስጦታቸው ሲናገር የመቄዶናዊያንን ምሳሌነት ነግሯቸዋል፡፡ በቁጥር 5 ላይ አስቀድመውም በእግዚአብሔር ፈቃድ ራሳቸውን ለጌታ ለእኛም ሰጡ እንጂ እንዳሰብን አይደለም በማለት ይናገራል፡፡ በጣም የሚያስገርመኝ ነገር ገንዘባቸውን ብቻ ሳይሆን ራሳቸውን ጭምር ሰጡ የሚለው ነው፡፡

በሮሜ 12፡1 ላይ ራሳችንን ለእግዚአብሔር መስዋዕት አድርገን ማቅረብ አለብን ይላል፡፡ ከቤተክርስቲያን ውጪ ለእግዚአብሔር መኖር ማለት ነው፡፡ ይህ ማለት ገንዘባችንን ለመስጠት ፈቃደኛ መሆን፣ በመንገዳችን ላይ እግዚአብሔር የሚያመጣውን ማንኛውንም ሰው ለመውደድ ፈቃደኛ መሆን ፣ ያለህን ማንኛውንም ሃብት ለእግዚአብሔር መንግስት ለማዋል ጭምር ፈቃደኛ መሆን ማለት ነው፡፡

ስለዚህ በሚቀጥለው ጊዜ ወደ ቤተክርስቲያን ስትመጡና የመባ ሳህኑ በአጠገባችሁ ሲዞር ለእግዚአብሔር ሁለንተናችሁን እንደምትሰጡት እንድትነግሩት አበረታታችኋለሁ!


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆይ ምንም ጥቅም በሌለው ሥጋዊ እውቀት በመፈለግ ጊዜዮን ማባከን አልፈልግም፡፡ ልክ እንደ ጳውሎስ ከምንም ነገር በላይ ቃልህንና አንተን በማወቅ የሚገኘውን መንፈሳዊ እውቀት እንደፈልግ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon