ሰላምን ለመለማመድ 6 መንገዶች

ከማስተዋልም በላይ የሆነው የእግዚአብሔር ሰላም፣ልባችሁንና ሀሳባችሁን በክርስቶስ ኢየሱስ ይጠብቃል፡፡ – ፊሊጲ 4፡7

በህይወት ለመደሰት በእግዚአብሔር ሰላም ውስጥ መኖር በጣም ዋና ነገር ነው፡፡በህይወታችሁ በሰላም ለመኖር አንዱ ቁልፍ ሰላምን ለማግኘት በየቀኑ ትንንሽ እርምጃዎችን መውሰድ ነው ብዬ አምናለሁ፡፡የበለጠ ሰላማዊ የህይወት ዘይቤን ለማዳበር ጥቂት ምክሮችን እነሆ፡፡

  • ሰአታችሁን የምታሳልፉበትን ነገር ምረጡ፡፡ ምናልባት ብዙ ነገሮችን ለማድረግ እየጣራችሁ መጨረሻ ላይ ግን አንዳቸውንም በደንብ ሳትሰሩ እየቀራችሁ ሊሆን ይችላል፡፡ችኮላ በመንፈስ ቅዱስ ከመመራት ይልቅ ስጋ ብዙ ሊሰራ ሲሞክር የሚፈጠር ነው፡፡በመንፈስ ተመሩ፡፡
  • መልካም በሆነ መንገድ “እምቢ” ለማለት ተዘጋጁ፡፡ አንዳንዴ እምቢ ማለት ስለሚከብደን ልናደርግ የማይገቡንን ነገሮች እናደርጋለን፡፡ማለት በሚገባችሁ ጊዜ እምቢ የምትሉባቸውን ቃላት እግዚአብሔር እንዲሰጣችሁ ጠይቁት፡፡
  • ነገ ታደርጉታላችሁ የሚልን መንፈስ ተቃወሙ፡፡ የእግዚአብሔር ቃል ራሳችንን በስርአት መምራትን እንድንለማመድ ይነግረናል፡፡ማረፍ ያለባችሁን ጊዜ በደንብ እንድትዝናኑበት የምታደርጉትን ነገር አሁን አድርጉት፡፡
  • ቁልፍ የሆኑ የሚያዘናጉ ነገሮችን አስወግዱ፡፡ አንዳንድ እንደ ቴሌቪዥን ያሉ የሚያዘናጓችሁን ነገሮች ካወቃችኋቸው ለራሳችሁ ጥቂት ደንቦችን አውጡ፡፡
  • ለሚያውኳችሁ ነገሮች ድንበሮችን አስቀምጡ፡፡ ሕይወት በሚያውኩ ነገሮች የተሞላ ስለሆነ በጤናማ መንገድ እንድትቆጣሯቸው የሚረዷችሁን እንደ ጊዜያችሁን ከፋፍሎ መጠቀም ያሉ ድንበሮች ማስቀመጥን መማር ትችላላችሁ፡፡
  • ህይወታችሁን አሻሽሉት፡፡ ጊዜን ለማትረፍ እና ከችግር ለመዳን እግዚአብሔርን ከመደበኛው አካሄድ የተለዩ መንገዶችን እንዲያሳያችሁ ጠይቁት፡፡ለምሳሌ እቃ ለማጠብ ጊዜ ሳጣ ከወረቀት የተሰሩ ሳህኖችን እጠቀማለሁ!

ዋናው ነገር ሰላምን ቅድሚያ ሰጥቶ ወደዛ ለመድረስ ተግባራዊ እርምጃዎችን መውሰድ እና እግዚአብሔር በእያንዳንዱ ቀን ፍጹም ወደሆነው ሰላሙ እንዲመራችሁ መፍቀድ ነው፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ማስተዋልን ሁሉ ወደሚያልፈው ወደ አንተ ሰላም ምራኝ፡፡ለእኔ ወዳየኸው ሰላም ለመራመድ በየቀኑ መውሰድ ያለብኝን እርምጃዎች አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon