ስለራስህ እዉነታዉን ተጋፈጥ

እኛን በሚቆጣጠር በእርሱ ዓይኖቹ ፊት ሁሉ ነገር የተራቆተና የተገለጠ ነው እንጂ፥ በእርሱ ፊት የተሰወረ ፍጥረት የለም።ዕብ 413

ንድ ሰዉ እኔ እንዴት ካለፈዉ ጥቃት ተላቅቄ እንደምኖር ጠየቀኝ፡፡ መልሴ እጅግ ቀላል ነበር፤ ስለራሴ እዉነታዉን እንድጋፈጥ እግዚአብሔር ጸጋዉንና ፈቃደኝነትን ሰጥቶኛል፡፡

እኔ ያደግሁት በቁጣ እና ባልተረጋጋ አካባቢ ነዉ፡፡ ቶሎ ተቆጪ ስለነበርኩ ብዙዉን ጊዜ እበሳጭ ነበር፡፡ ብስጩ በመሆኔ በመከፋትና በተስፋ መቁረጥ ነዉ ያደግሁት፡፡ የተሸለ ህይወት ኖሮኝ ቢሆን ምኞቴ ነበር ነገርግን ምኞቴ ምንም አልፈታልኝም፡፡ የቤተሰቦቼን ክፉ የኋላ ታሪክ እያነሳሁ ችግሮቼን በእነሱ መዉቀስ ጊዜዬን ነዉ የበላብኝ፡፡

በመጨረሻም ባለፈዉ ታሪኬ ስለተፈጸመዉ ክፉ ነገር እኔ ተጠያቂ እንዳልሆንኩና ካለፈዉ ምንም መቀየር እንደማልችል እንዳስታዉስ እግዚአብሔር ረዳኝና ስላለፈዉ ጊዜ ቢሆን ኖሮ እያልኩ መመኘት አቁሜ ወደፊት መጓዝ ጀመርሁ፡፡ በዙሪያዬ ያሉ ሰዎችን እና ሁኔታዎችን መዉቀስና ራሴን ማታለል ማቆም ነበረብኝ፡፡ ይህንን ሳደርግና እንድፈዉሰኝና እንዲያድሰኝ እምነቴን በእግዚአብሐየር ላይ መጣል ስጀምር ተለወጥኩኝ፡፡ አሁን በህይወቴ ሰላምና ፍሰሃ አለ፡፡

አንተም በተመሳሳይ ሁኔታ ዉስጥ ትኖር ይሆናል፡፡ ስለራስህ ያለዉን እዉነታ መጋፈጥ ሊያስፈራ ይችላል ግን ይህን ብቻህን ማድረግ የለብህም ፡፡ ሁሉም ነገርህ በእግዚአብሔር ፊት የተጋለጠ ነዉ፤ ሀሳቡን እንዲገልጥልህ ብትጠይቀዉ እርሱ ራስህን ከፍ እንድታደርግና እንድትቀበል፣ ሐላፊነት እንድትወስድና ሰላማዊ ህይወት እንድትኖር ይረዳሃል፡፡ ዛሬ ስለራስህ እዉነታዉን ለመጋፈጥ አትፍራ ግን እግዚአብሔር ወደ አዲስ ነገ ይምራህ፡፡

የጸሎት መጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ! ስለራሴ እዉነታዉን ለመጋፈጥ የአንተን እርዳተ እፈልጋለሁ፡፡ ይህ ጊዜ የለፈዉን ህይወቴን ችግርና ሰዎችን የመዉቀሻ አይደለም ስለዚህ እንድተዉ በሐይልህ አግዘኝ፡፡ ሐላፊነት እንድወስድና ወደ ተሸለዉ እንድለወጥ እርዳኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon