ስሜቶቻችሁን መቆጣጠር

እግዚአብሔር አምላክሽ በመሀከልሽ አለ፤እርሱ ብርቱ ታዳጊ ነው፤ – ሶፎ 3፡17

ከስሜቶች ጋር መታገል የህይወት እውነታ ነው፡፡እስከኖርን ድረስ የተለያዩ ስሜቶችን እና ምላሾችን እናስተናግዳለን፣ እናም መኖራቸውን መካድ ወይም በእነርሱ የተነሳ የጥፋተኝነት ስሜት ሊሰማን አይገባም፡፡

ነገር ግን ስሜቶቻችንን መቆጣጠር መማር ይገባናል፡፡ልናምናቸው እንደማይገባ ስንረዳ ይሄ ቀላል ይሆናል፡፡እንደ እውነቱ ከሆነ እንደውም ዋናው ጠላታችን ሊሆን ይችላል፡፡ሰይጣን በመንፈስ እንዳንጓዝ ለማድረግ ስሜቶቻችንን በእኛ ላይ ይጠቀማል፡፡

በእያንዳንዳችን ውስጥ ያደረው ጌታ ሀያል መሆኑን ማወቅ እጅግ አስፈላጊ ነው፡፡በውስጣችን ያለው ሀይሉ ስሜቶቻችንን እንድናሸንፍ አስችሎ ከሚለዋወጠው ስሜታችን ይልቅ  በማይለዋወጠው ቃሉ እና መንፈሱ እንድንመራ ያደርገናል፡፡

መንፈሳዊ መረጋጋት እና የስሜት ብስለት በተፈጥሮ የሚመጣ ነገር አይደለም፡፡በሙሉ ልባችሁ ልትፈልጉትና ለማግኘት ቁርጠኛ ልትሆኑ ይገባል፡፡መንፈሳዊ መረጋጋትን ቀዳሚ ነገር ስታደርጉ ስሜቶቻችሁን እንድትቆጣጠሩ ሊረዳችሁ እግዚአብሔር ከፈቃደኛም በላይ ነው፡፡

ዛሬ ይሄንን እንድትከታተሉ አበረታታችኋለሁ፡፡መንፈሳዊ መረጋጋትን፣  ደስተኛ፣ እና በድል የተሞላ ህይወትን ተደሰቱበት!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ መንፈሳዊ መረጋጋትን ለመከታተል መርጫለሁ፡፡በስሜቶቼ ቁጥጥር ስር መዋልን አልፈልግም፣  ይልቁንስ በሚገባ እነርሱን ማስተዳደርን እንጂ፡፡በውስጤ ስለምትኖር እና በታላቁ ሀይልህ ስለምትረዳኝ አመሰግናለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon