ቀላል የሆኑ ልዩ መብት

ቀላል የሆኑ ልዩ መብት

የእግዚአብሔር ሕግ ፍጹም ነው ነፍስን ይመልሳል፤ የእግዚአብሔር ሥርዓት ቅን ነው ልብን ደስ ያሰኛል፡፡ መዝ፡ 19÷7

ከእግዚአብሔር ጋር ተቀራርበው ከመነጋገርና ከመስማት የበለጠ ታላቅ ክብር ያለ አይመስለኝም፡፡ ፀሎት በሕይወታችን በጣም ወሳኝ የሆነ ልዩ መብታችን እንደሆነ አምናለሁ፡፡ ፀሎት ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት በማድረግ እራሳችንና የምንወዳቸውን ሰዎች እያንዳንዳችን በምናልፍበት ጎዳና የእግዚአብሔርን ዓላማና ዕቅድ የምንከተልበትና የጠላትን ዓላማና ዕቅድ ደግሞ የምንመክትበት መንገድ ነው፡፡ እኛ የሰው ልጆች በምድር ላይ ሆነን ወደ እግዚአብሔር መገኘው ውስጥ የምንገባበት ልዩ መንገድ ነው፡፡ የልባችን ሃሣብ ለእግዚአብሔር የምናካፍልበት አጋጣሚና የእርሱን ድምፅ ለመስማት ያስችለናል፡፡ እግዚአብሔር ለእኛ ያለውን ትልቅ ነገር ተረድተን ደስ እንዲለን ይረዳናል፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብረት ማድረግ ከሁሉም የሚበልጥ ትልቅ እድል እንደሆነ አስባለሁ፡፡ ነገር ግን ይህ ሲጀምር ከእግዚአብሔር ጋር መነጋገርና ድምፅን መስማት ይህን ያህል በጣም ውስብስብ አይደለም፡፡ ልክ እንደማንኛውም ተፈጥሮአዊ ነገሮች ቀላልና ከእርሱ ጋር ሁልጊዜና ሁልቀን መጠበቅና ኅብረት ማድረግ እንችላለን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ልክ አየር እንደምትተነፍስ ፀሎትንም ፀልይ፡፡ ቀኑን በሙሉ ልክ እንደተፈጥሮአዊ ሒደቶች በቀላሉ አድርግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon