በለሆሳስ የምትሰማውን ድምጽ መከተል

ወደ ቀኝም ሆነ ወደ ግራ ዘወር ብትል ጆሮህ ከኋላህ፣መንገዱ ይህ ነው፤ በእርሱ ሂድየሚል ድምፅ ይሰማል። – ትንቢተ ኢሳያስ 30፡21

ንፈስ ቅዱስ ዘወትር በሕይወት ጉዞኣችን ሊመራን ይፈልጋል፡፡ አንዳዴ የሚናገረን በለሆሳስ ድምፅ በመሆኑ ትልቅ የሚመስሉንን ነገሮች ላይ ትኩረት በማድረጋችን አናስተውልም፡፡ አንድ ቀን ወደ ቤቴ እየሄድኩ ፣ ቆም ብዬ ቡና ለመጠጣት ፈለግሁ፡፡ አብራኝ የምትሰራ ረዳቴ ጋር ደውዬ ቡና መጠጣት እንደምትፈልግ ለመጠየቅ ግድ አለኝ፡፡  ስደውልላት ረዳቴ ‹‹ቡና ለመጠጣት እያሰበች እንደሆነና ወዲያውኑ ጥሩ ቡና እንደሚስፈልጋት ነገረችኝ››፡፡

አያችሁ እግዚአብሔር የልቧን መሻት ሊያደርግላት በእኔ ውስጥ ሆኖ እየሰራ ነበር፡፡ ታላቅ የሆነ ድምጽ አልሰማሁም ፤መልኣክም ቆሞ አልታየኝም፡፡ በውስጤ ግን አንድ ስሜት ወይም ሀሳብ ቡና እንድጋብዛት ተሰማኝ፡፡

በተመሳሳይ እግዚአብሔር በእኛ ሕይወት ሰዎችን ሊባርክ ይፈልጋል፡፡ ልባችሁ ለእግዚአብሔር ድምጽ ንቁ እንዲሆን ዛሬ አበረታታችኋለሁ፡፡ በለሆሳስ የሚመጣውን ግፊት ተከተሉ፡፡ ለልባችሁ ይናገራል መሄድም ያለባችሁን መንገድ ይመራችኋል፡፡

ጸሎት ማስጀመሪያ

መንፈስ ቅዱስ ሆይ ዛሬ እኔ ዝም ብዬ አንተን ደግሞ በለሆሳስ ስትናገር ለመስማት መርጫለሁ፡፡ እባክን ሌሎችን በእኔ የሚባረኩበትን መንገድ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon