በለዉጥህ ተደሰት

በለዉጥህ ተደሰት

ሕግህ ለእግሬ መብራት፥ ለመንገዴ ብርሃን ነው። – መዝ 119፡105

ሁላችንም ለማደግና ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን ግንኙነት ለማሻሻል ዕድል አለን፡፡ መሄድ ስለሚገባኝ ርቀት ባሰብኩ ጊዜ ተስፋ እቆርጥ ነበር፤ በየቀኑ አንዳንዴም በየሰዓቱ ማስታወስ ያለብኝ ይመስለኝ ነበር፡፡ ዘላቂ የሆነ የውድቀት ስሜት ተሸክሜ ነበር፤ መሆን ያለብኝን ሰዉ እንዳልሆንኩ፣ ጥሩ እየሰራሁ እንዳልሆነና እንደገና መሞከር እንደሚያስፈልገኝ አስብ ነበር፡፡ ሆኖም ግን እንደገና ስሞክር ድጋሚ እወድቅ ነበር፡፡

አሁን አዲስ አመለካከት ወርሼአለሁ፡፡ መሆን የሚገባኝ ቦታ ላይ አይደለሁም እግዚአብሔር ይመስገን በነበርኩበትም ቦታ አይደለሁም፤ ደህና ነኝ መንገዴ ላይ ነኝ! መድረስ የሚገባኝ ቦታ ስላልደረስኩ እገዚአብሔር እንደማይቆጣኝ አሁን አዉቄአለሁ፡፡ እርሱ ባዛጋጀልኝ መንገድ ላይ ስላለሁና እየተጓዝኩም ስለሆነ እርሱ ይደሰታል፡፡

እናንተና እኔ በመጓዝ ላይ ብንቀጥል እግዚአብሔር በለዉጣችን ይደሰታል፡፡ መንገዳችንን ሊያበራልን ቃል ገብቶአል፡፡ መንገዱን አናዉቀዉ ይሆናል ከጊዜ ወደ ጊዜ እንቅፋት ይበዛብንም ይሆናል እግዚአብሔር ግን ታማኝ ነዉ፡፡ ለዉጥህን ያያል፣ በአንተ ይኮራል ፤ ሊረዳህም ይመጣል ስለዚህ በትክክለኛዉ ጎዳና ቆይ!


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ስላለሁበት ቦታ ተስፋ መቁረጥ አልፈልግም፤ እስከዚህ አምጥተሀኛል ደግሞም መንገዴን ማብራትህን እንደምትቀጥል አዉቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon