በልቡ ንፁህ የሆነው እግዚአብሔርን ያየዋል

በልቡ ንፁህ የሆነው እግዚአብሔርን ያየዋል

ልባቸው ንጹሕ የሆነ ብፁዓን ናቸው፤ እግዚአብሔርን ያዩታልና። (ማቴዎስ 5: 8)

ንፁህ ልብ ካለን እግዚአብሔርን በግልፅ መስማት እንችላለን። ለህይወታችን እቅዱን በግልፅ እናያለን። ዓላማ የለሽ ወይም ግራ መጋባት አይሰማንም። የልባችን ሁኔታ ለእግዚአብሔር በጣም አስፈላጊ ከሆኑት ነገሮች አንዱ ነው። የተሰወረው የልብ ሰው በትክክለኛው ሁኔታ ከተቀመጠ እግዚአብሔርን እጅግ ያስደስተዋል (1 ጴጥሮስ 3፡3–4ን ተመልከት) ። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው ልባችንን በሙሉ ትጋት ልንጠብቅ ይገባል፣ ምክንያቱም የሕይወት ጉዳዮች ሁሉ ከእርሱ ይወጣሉና (ምሳሌ 4፡23ን ተመልከት) ።

እግዚአብሔር የማይደሰትበት ነገር ካለ ለማየት ልብህን፣ ውስጣዊ አመለካከትህን እና ሀሳብህን መርምር። ምሬት አልያም ቂም አለህ? የትችት ወይም የፈራጅነት አመለካከት ስር እንዲሰድ ፈቅደሃል? ልብህ ለስላሳ ነው ወይስ ጠንካራ? ለሌሎች አስተያየቶች እና ሀሳቦች ክፍት ነህ ወይስ ልብህን ዘግተኸዋል? መጽሐፍ ቅዱስ ልባችንን በተገቢው ሁኔታ የመጠበቅ እና የመከላከል ኃላፊነት እንዳለብን ይናገራል።

አካላዊው ልባችን በሰውነት ውስጥ በጣም አስፈላጊ አካል ነው። ከታመመ ወይም በተገቢው መንገድ እየሠራ ካልሆነ በሕይወት እና በሞት መካከል ያለውን ልዩነት ሊያመለክት ይችላል። ትኩረት ልንሰጣቸው ከሚገባን በጣም አስፈላጊ ነገሮች ውስጥ አንዱም የልባችን አመለካከት ነው ብዬ አምናለሁ። በበሽታ ወይም ተገቢ ባልሆነ ነገር እንዲሞላ ከፈቀድንለት በእርግጠኝነት የህይወታችንን ጥራት ይጎዳል።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ መለወጥ የምትፈልጋቸውን ማንኛቸውንም የልብ ሁኔታዎች (የልብ ዝንባሌዎች) እንዲያሳይህ ዛሬ ደግሞም በየቀኑ እግዚአብሔርን ጠይቅ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon