በመንፈስ ሆነህ አዳምጥ

በመንፈስ ሆነህ አዳምጥ

ነፋሱ ወደሚፈልገው ይነፍሳል፤ ምንም እንኳን ድምጹን ብትሰማዉም፣ ከየት እንደመጣ ወይም ወዴት እንደሚሄድ አታውቅም። ከመንፈስ ለተወለዱ ሁሉ እንዲሁ ነው። (ዮሐንስ 3: 8)

ዳግመኛ ስንወለድ በመንፈሳችን ሕያዋን እንሆናለን ደግሞም ለእግዚአብሔር ድምፅ የነቃን እንሆናለን። ከየት እንደመጣ መናገር ባንችልም እንኳን ሹክሹክታውን እንሰማለን። ሊወቅሰን ሊያርመን ደግሞም ሊመልሰን በልባችን ውስጥ በዝግታና በተረጋጋ ድምፅ ይናገረናል። ከሰዎች ጋር ለመግባባት አፋችንን፣ የፊት ገጽታችንን እንዲሁም የሰውነት እንቅስቃሴአችንን ልንጠቀም እንችላለን፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔርጋር መነጋገር ስንፈልግ በመንፈሳችን በኩል ነው።

እግዚአብሔር ለውስጣዊ ማንነታችን በቀጥታ ህብረት በማድረግ ውስጥ፣ በመገለጥ ደግሞም በህሊናችን (በመሰረታዊነት ትክክልና ስህተት በምንላቸው ጉዳዮች አማካኝነት) እና በሰላም ዉስጥ ይናገረናል። መንፈሳችን ተፈጥሮአዊው አእምሯችን የማይገነዘባቸውን እና ሊረዳቸው የማይችላቸውን ነገሮች ማወቅ ይችላል።

ለምሳሌ፣ ለእግዚአብሔር ድምፅ ንቁዎች ስንሆን፣ ትክክል የሚመስልን ሁኔታ አይተን በውስጣችን ግን የሆነ ትክክል ያልሆነ ነገር በዉስጡ እንዳለ እንረዳለን። ያ በመንፈሳችን ውስጥ ያለው “መረጋገጫ” እኛ ከማይመስለን ሰው ጋር እንዳንተባበር ወይም ልንሳተፍበት በማይገባን ነገር ውስጥ እንዳንገባ ለማድረግ የታሰበ ነው።

በልብህ ውስጥ ለሚከብዱ እና በመንፈስህ ለምትገነዘባቸው ነገሮች ትኩረት ስጥ፤ ምክንያቱም እዚያ ውስጥ ነው እግዚአብሔር ለአንተ የሚናገራቸው የምሪት፣ የማበረታቻ፣ የማስጠንቀቂያ እና የማጽናኛ ድምፆች የሚገኙት።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ በመንፈስህ ውስጥ ለሚገኙት ማረጋገጫዎች ትኩረት ስጥ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon