በመንፈስ ሕያው ሁን

በክርስቶስ ኢየሱስ ያለው የሕይወት መንፈስ ሕግ ከኃጥያትና ከሞት ሕግ አርነት አውጥቶኛልና፡፡ ሮሜ 8 2

እኛ በራሳችን ኃይልና መንገድ ሕግን ሁሉ በመጠበቅና ኃይማኖተኛ በመሆን ከእግዚአብሔር ጋር ሕብረት ለመፍጠር ስንሞክር በከፋ ሁኔታ እንወድቃለን፡፡ እንዲሁም ደግሞ እንሸነፋለን፡፡ ኢየሱስ በእኛ ፈንታ ሕግን ሙሉ በሙሉ በትክክል ፈጽሞ የእኛን የኃጥያት ዕዳ በመክፈል በደላችንን ደመሰሰ፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር የምንገኝበት መንገድ በእምነትና በስሙ በኩል አድርጎ በሥራችን ለመጽደቅ መታገልን ከእኛ ላይ አነሣ፡፡

ኢየሱስ ማንም የሚወደኝ ቢኖር ቃሌን ይጠብቃል ትዕዛዜንም ይቀበላል አለ፡፡ (ዮሐ. 14 15 ተመልከት0 ቃሌን ሁሉ ብትጠብቁ እወዳችኋለው አላለም፡፡ እግዚአብሔር ቀድሞ እኛን ወዶናል፡፡ እኛም የድርሻችንን በመወጣት ለፍቅሩ ምላሽ የሚሆን መታዘዛችንን መግለፅ አለብን፡፡ በተጨማሪም እርሱ እንድናውቅ የምፈልገው በተሳሳትን ጊዜ ሙሉ በሙሉ ምህረት መቀበል እንደምንችል ነው፡፡

በብሉይ ኪዳን ሥር ኃጥያት ሞትን ያመጣል ወይም ያስከትላል፡፡ ነገር ግን የፍቅር ሕግ አሁን የምንኖርበት ሕይወትን ለእኛ ያመጣል፡፡ የእግዚብሔር ፍቅር የሚገርምና ነገሮችን ሁልጊዜ በትክክል ያለአንዳች ግድፈት እንድንፈፅምና በዚያ ጉዳይ እንዳንጨናነቅ ሳይሆን በእርሱ መገኘት ውስጥ እራሳችንን ለቀቅ እንድናደርግና የእርሱን ድምፅ እንድንሰማ ነው፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ኢየሱስ በመስቀል ላይ የሠራው ከእግዚአብሄር ጋር ኅርት እንድታደርግ ነገሮችን ምቹ አድርጎልሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon