በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ

በመንፈስ ቅዱስ መጠመቅ

እንኪያስ እናንተ ክፉዎች ስትሆን ለልጆቻችሁ መልካም ስጦታ መስጠት ካወቃችሁ በሰማይ ያለው አባት ለምለምኑት እንዴት አብልጦ መንፈስ ቅዱስን ይሰጣቸው; ሉቃ 11 13

የዛሬው ጥቅል እግዚአብሔር ለምለምኑት መንፈስ ቅዱስን ለመስጠት ተስፋ የገባበት ነው፡፡ አሁን በዚህ ሰዓት እግዚአብሔር በመንፈስ ቅዱስ እንደምላህና እንድያጠምቅህ ልትጠይቀው ትችላለህ አሁን ባለህበት ቦታ ሆነህ እንዲህ ብለህ መፀለይ ትችላለህ፡፡

‹‹አባት ሆይ በመንፈስ ቅዱስ እንድታጠምቀኝና ማረጋገጫና ምልክቶች እንዲከተሉኝ እፀልያለሁ፡፡ በጴንጤ ቆስጤ ዘመንለነበሩት ሰዎች እንዳደረክ በድፍረትና በኃይል ሙላኝ፡፡ እንዲሁም የመንፈስ ቅዱስ ፀጋ ስጦታ እንደፈቃድህ ስጠኝ፡፡››

አሁን ‹‹በመንፈስ ቅዱስ እንደተሞላው አምናለሁ፡፡ እና ተመልሼ እንደቀድሞ አልሆንም›› በማለት በታላቅ ድምፅ እምነትህን ማጽናት ትችላለህ፡፡

ከላይ ያለውን ፀሎት የፀለይክ እንደሆነ ወይም ተመሳሳይ ፀሎትም ብሆንም በፀጥታ ውስጥ ሆነህ በፀሎት የጠየከውን በእምነት እንደተቀበልክ በማመን ጠብቅ፡፡ እንደተቀበልክ በእምነት ካልወሰድከው ምንም እንኳ ተቀብለህ ሳለህ እንኳ በእምነት እንዳልተቀበለ ሰው እንዲያው ይሆናል፡፡ በማጠንከር መናገር የምፈልገው በእምት መቀበልን ማመን በጣም አስፈላጊ እንደሆነ እንጂ የእራሴን ውሳኔ በሚሰማንና በሚመስለን ላይ አለማድረግ ነው፡፡ ቀኑን ሁሉ በእርግጥ እግዚአብሔር በአንተ ውስጥ እንደሚኖርና በእርሱ ደግሞ ለማድረግ የፈለከውን ማድረግ እንደምትችል አሰላስል፡፡

በአማኝ ሕይወት ውስጥ ከሚፈፀሙ ነገሮች ውስጥ በጣም ጥሩ ከሆኑ ነገሮች ውስጥ አንዱ በመንፈስ ቅዱስ መሞላት ነው፡፡ የእርሱ መገኘት ድፍረት፣ ተስፋ፣ ሠላም፣ ደስታ፣ ጥበብ እና የተለያዩ በጣም ጥሩ ነገሮች ይሰጣል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔርንና የእርሱን መገኘት መፈለግህን እርግጠኛ ሁን እንጂ እርሱ ለሚያደርግልህ መልካም ነገሮች ላይ አይደለም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon