በመከራው ተካፋይ መሆን

በመከራው ተካፋይ መሆን

የአሁኑ ዘመን ሥቃያችን ወደ ፊት ሊገለጥ ካለው ለእኛ ከተጠበቀልን ክብር ጋር ሲነጻጸር ምንም እንዳይደለ እቈጥራለሁ። – ሮሜ 8፡18

እንደ ክርስቲያን የክርስቶስ የክብሩ ተካፈዮች መሆናችንን ተምረናል እናውቃለንም ይሁንና በመከራውስ ተካፋዮች ነን? የክርስቶስ መስዋዕትነት የዘላለም ህይወት ነው በዚህም በምድርላይ ስንኖር የሚበዛ ህይወትን አጎናፅፎናል፡፡ነገርግን መፅሀፍ ቅዱስ የክብሩ ተካፋዮች የሆነውን ያህል መከራውም ተካፋዮች እንድንሆን ይናገራል፡፡

ባለንበት ሁኔታ የተነሳ መከራ ሊደርስብን እንደሚችል ይሰማናል ነገርግን መፅሐፍ ቅዱስ ሁኔታዎቻችን መልካም ባይሆኑም እንኳ ትክክለኛውን ነገር እንድናደርግ ያዘናል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እምነታችንን ያሉብን ችግሮች ለማራቅ እንጠቀምበታለን ነገርግን እግዚብሔር እምነታችንን በእንደዚህ አይነት ሁኔታዎችም ውስጥ እንድንለማመደው ለማድረግ በመከራ ተካፋዮች እንድንሆን ያደርገናል፡፡

ሁልጊዜ እግዚብሔር በፀናች ክንዱ የሚያደርገውን ተዓምራት እንከታተላለን ነገርግን የሚያስችለንን ፤ የሚጠብቀንንና የሚያበረታንን ኃሉን ግን አሳንሰን እናየዋለን፡፡ኢየሱስ በዮ 16፡33 ላይ በመከራችን ወቅት ሰላሙን እንደሚሰጠን እንደሚያበረታንና ችግራችንንም እንድናሸንፈው የሚያስችለንን ኃይል እንደሚሰጠን ቃል ገብቶልናል፡፡ ዛሬ በምንም መከራ ውስጥ እያለፋችሁ ከሆነ ልባችሁን በክርስቶስ ላይ እንድታደርጉ አበረታታችኋለሁ፡፡ በመከራም በመፅናት የእሱ የክብሩ ተካፋዮች ትሆናላችሁ፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚብሔር ሆይ ሮሜ8፡18 እንደሚናገረው አሁን ለጥቂት ጊዜ የገጠመን መከራና ፈተና ሊገለጥ ካለው ክብር ጋር ሲነፃፀር ምንም እንዳልሆነ` ይናገራል፡፡ ይህን ግንዛቤ መያዝ እፈልጋለሁ ስለሰላምህና ስለኃይልህ አመሰግንሃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon