በመጠን እና በእርካታ መኖር

ነገር ግን እውነተኛ መንፈሳዊነት ባለን ነገር ከመርካት (የውስጥ ብቁነት ሰሜት ነው) ጋር ትልቅ ትርፍ ነው፡፡ – 1 ኛ ጢሞ 6፡6

መጽሀፍ ቅዱስ ሲናገር እግዚአብሔርን መምሰል ከእርካታ ጋር ታላቅ ትርፍ ነው ይላል፡፡በእርካታ የሚኖር የእግዚአብሔር ሰው መገኘት ከሚችልበት ምርጡ ቦታ ላይ ነው ያለው፡፡

ደስታ የሚመጣው ነገሮቻችሁ ሁሉ በትክክል ሲሄዱ እና በቁጥጥር ስር ሲሆኑ አይደለም፡ይልቁንስ ከልባችሁ ውስጥ ነው የሚመጣው፡፡ለምሳሌ አለም የተሞላችው ያስፈልገኛል ብለው የሚያምኑት ነገር ሁሉ ባላቸው ነገር ግን ደስተኛ ባልሆኑ ሰዎች ነው፡፡እንደውም በአለም ላይ በጣም ደስተኛ ካልሆኑት ሰዎች መካከል ሁሉም ነገር ያላቸው የሚመስሉት ናቸው፡፡

እርካታ ከእውቅና ፣ከዝና፣ካላችሁ የገንዘብ መጠን፣በስራ ስፍራ ከሚሰጣችሁ ቦታ ወይም አብሯችሁ ከሚያሳልፉት ሰዎች ማንነት ጋር የተገናኘ አይደለም፡፡እርካታ በትምህርት ደረጃችሁ ወይም በተወለዳችሁበት ነገር ውስጥ አይገኝም፡፡እርካታ ልብ ውስጥ ያለ አመለካከከት ነው፡፡

ከእውነተኛ አመስጋኝ ሰው የሚበልጥ ደስተኛ ሰው የለም፣አውነተኛ እርካታን የሚያውቅ ሰው እርሱ ነው፡፡መርካት የሚለው የቃሉ ትርጉም “ከመርካታችሁ የተነሳ ምንም ቢካሄድ ወደማትረበሹበት ደረጃ መድረስ ሲሆን ምንም ለውጥ ማድግ እስከማያስፈልጋችሁ ድረስ መርካት ግን አይደለም፡፡”

ሁላችን ነገሮች ሲሻሻሉ ማየት እንፈልጋለን፡፡አሁን ያላችሁበት ደረጃ ግን ሊረብሻችሁ አይገባም፡፡እግዚአብሔር በስራ ላይ እንዳለ እና ነገሮች እየተለወጡ እንዳሉ ለማመን መምረጥ ትችላላችሁ፣ እናም ውጤቱን በጊዜ ሂደት ታዩታላችሁ፡፡

ህይወት ሙሉውን በምንመርጣቸው ምርጫዎች የሚወሰን ነው…ስለዚህ በየቀኑ ያለኝ ይበቃኛል ማለትን እና እርካታን ምረጡ፡፡ይሄን በማድረጋችሁ አትሳሳቱም፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ያለኝ ይበቃኛል የምል እና በእርካታ የምኖር ሰው መሆን እፈልጋለሁ፡፡በየቀኑ እርካታ ያለኝ ሰው ለመሆን እንድመርጥ አቅሙን ስጠኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon