
ኃይልን በሚሰጠኝ በእርሱ ሁሉን ማድረግ እችላለሁ፡፡(ውስጣዊ አቅምን በእኔ ውስጥ በሚጨምረው በእርሱ ለማናቸውም ነገር ዝግጁ እና ከማናቸውም ነገር ጋር እኩል ነኝ፡፡በክርስቶስ ብቃት በራሴ በቂ ነኝ፡፡) – ፊሊጲ 4፡13
ፊሊጲሲዩስ 4፡13 ከአውድ ውጪ ከሚጠቀሱ ጥቅሶች መሀከል ዝነኛው ነው፡፡” ሀይልን በሚሰጠኝ በክርስቶስ ሁሉን እችላለሁ” ነው የሚለው፡፡ይሄ ማለት ስለፈለጋችሁ ብቻ የወሰናችሁትነ ሁሉ ማድረግ ትችላላችሁ ማለት አይደለም፡፡ጳውሎስ በተለይ ሲናገር የነበረው በምንም አይነት ሁኔታ ውስጥ ቢያልፍ በክርስቶስ ሀይል እንዴት እርካታ ሊኖረው እንደቻለ ነው፡፡
በእግዚአብሔር ጸጋ በህይወታችን ማድረግ የፈለግነውን ሁሉ ማድረግ እንችላለን ብዬ አምናለሁ፡፡ሊኖረን የሚገባው አመለካከት ይሄ ይመስለኛል፡፡በእግዚአብሔር የምትታመኑ ከሆነ የሚከብዳችሁ ነገር አይኖርም፡፡እግዚአብሔር ከምንችለው በላይ እንደማንፈተን የተስፋ ቃል ስለሰጠን በመንገዳችሁ የሚመጣውን ማናቸውንም ነገር ትችሉታላችሁ፡፡
አሁን ያላችሁበት ሁኔታ ምንም ሆነ ምን በህይወታችሁ የሚካሄደውም ነገር ምንም ሆነ ምን አዎንታዊ አመለካከትን ያዙ፡፡ፈታ በሉ-እግዚአብሔር የእናንተ ወገን ነው፡፡ምንም ልታደርጉ ስለማትችሏቸው ነገሮች መበሳጨታችሁን አቁሙ፡፡
እግዚአብሔር ለህይወታችሁ ግላዊ እቅድ እንዳለው እንድታውቁና ልዩ የሆነውን እቅዱን እንድትቀበሉ ከሌላም ሰው ጋር እንዳታወዳድሩት ይፈልጋል፡፡እግዚአብሔር ስለምትፈልጉት ነገር እና ልትችሉት አቅማችሁ ስለሚፈቅደው ነገር ከእናንተ በላይ እንደሚያውቅ እመኑት፡፡ደግሞም ራሳችሁን ከምታውቁት በላይ እናንተን የሚየውቃችሁ እርሱ ነው፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆይ ልክ እንደ ጳውሎስ እርካታዬ ከሁኔታዎች ሳይሆን ከአንተ እንዲመጣ እፈላጋለሁ፡፡ለእኔ ያለህ እቅድ ፍጹም መሆኑን እና መጨነቅ እንደሌለብኝ በየዕለቱ አሳየኝ፡፡