በረከት አያምልጥህ

በረከት አያምልጥህ

«እግዚአብሔርን ዘወትር የሚፈራ ሰው ቡሩክ ነው፤ ልቡን የሚያደነድን ግን መከራ ላይ ይወድቃል» (ምሳ. 28፡14)።

እግዚአብሔር በተለያዩ ዓይነት መንገዶች ለእኛ ይናገራል፤ ነገር ግን ልባችንን ብናደነድንና እርሱ የሚናገረውን ለመታዘዝ እምቢታ ካሳየን እርሱ ሊሰጠን የሚፈልገውን በረከት ሳናገኝ ያመልጠናል ወይም ከበረከቱ እንጎድላለን። እኔ እግዚአብሔር እንዳደርገው የሚፈልገው ትንሽ ነገር ያዘዘኝን ጊዜ እንኳን ላስታውስ እችላለሁ፣ ወይም እርሱ የማይፈልጋቸውን እኔ ሳደርጋቸው የነበሩትን ነገሮች በእኔና እርሱ መካከል ትግል የሚፈጥሩ ሆነው አገኛቸው ነበር። እግዚአብሔር እንዳደርጋቸው እኔን የሚጠይቃቸውን ነገሮች ተስማምቼ ከመቀበሌ በፊት የእርሱን ሃሳብ ለማስቀየር ቀናትን፣ ሳምንታትን፣ ወራትንና አንዳንድ ጊዜ ዓመታትን ጭምር በመውሰድ እግዚአብሔር ከእኔ ጋር ይሟገታል።

እኔም በመጨረሻ ለእርሱ ሃሳብ ተሸንፌ እጅ ስሰጥ እኔ ከምገምተው በላይ ነገሮች ለእኔ መልካም ሆነው ይሰራሉ። ለመጀመሪያ ጊዜ እግዚአብሔር ማድረግ የሚገኝን እንዳድርግ ሲጠይቀኝ በቀላሉ በመታዘዝ ሳደርግ ራሴን ከብዙ ችግሮች ለማዳን ችያለሁ።

የራሳችን መንገዶች የማይሰሩ ቢሆኑም እንኳን አብዛኞቻችን በራሳችን መንገድ በወሰነው ውሳኔ ግትሮች ነን። ይሁንም እንጂ ለእግዚአብሔር ልባችን ክፍትና ለሚናገረን ድምጽና ለመንፈስ ቅዱስ ምሪት ንቁ ሆኖ መገኘትን ልንማር እንችላላን። መንፈሳችን የተሰራው ከእግዚአብሔር ጋር ህብረት ሊያደርግ እንዲችል ተደርጎ ነው። እርሱ ለውስጣው ማንነታችንና ለህሊናችን በኩል ከመከራ ሊጠብቀን ይናገረናል እንዲሁም መልካሙንና ክፉውን እንድለይ ሊያሳውቀን ይፈቅዳል። ከዚያም በመንፈሱ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ እንድንችል ይረዳናል።

እኔ ዛሬ የማደፋፍርህ ከግትርነት ህይወት ወጥተህ ወደ እግዚአብሔር እንድትመለስና ድምጹን ለመስማትና ለመታዘዝ በመፈለግ በተከፈተ ልብ ከእርሱ ጋር እንድትራመድ (እንድትመላለስ) አበረታታሃለሁ።


ላንተ የሆነው የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል፡ በራስህ ጎዳና ከመራመድ በእግዚአብሔር መንገድ መጓዝ ከሁሉም የተሻለ ነው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon